የምርጫ ቦርድ ለመገናኛ ብዙኃን የዘገባ ፈቃድ እየሰጠ ነው
ሐሙስ፣ መጋቢት 30 2013ማስታወቂያ
ከሁለት ወራት ያነሰ ጊዜ የቀረውን ስድስተኛውን ጠቅላላ አገር አቀፍ ምርጫ ለመዘገብ እስካሁን ሃያ አንድ የሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃንና 800 ጋዜጠኞች የዘገባ ፈቃድ መሰጠቱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ አስታውቋል። መስፈርቱን ለሚያማሉ ቀሪ የመገናኛ ብዙኃን እና ጋዜጠኞችም በቀጣይም ፈቃድ መስጠቱን እንደሚቀጥል ቦርዱ ገልጿል።
መገናኛ ብዙኃኑ የመረጃ ፍሰት እጥረት እንዳይገጥማቸው የሚዲያ ማዕከላት በቀጣይ ቀናት ተከፍተው አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ እያመቻቸ መሆኑንም ነው ቦርዱ በተለይ ለዶይቼ ቬለ የገለጸው። ፍቃድ የተሰጣቸው የመገናኛ ብዙኃኑ ኃላፊነት በተሞላበትና ከፍተኛ ጥንቃቄ ባለው መልኩ መረጃዎችን ለሕዝብ እንዲያቀርቡ ይደረጋልም ተብሏል።
ሰለሞን ሙጬ
ታምራት ዲንሳ
ኂሩት መለሰ