የማይካድራ ጭፍጨፋ ተጠርጣሪዎች
ሐሙስ፣ የካቲት 18 2013ማስታወቂያ
ማይካድራ-ትግራይ ዉስጥ ባለፈዉ ጥቅምት በሠላማዊ ነዋሪዎች ላይ በተፈፀመዉ ጭፈጨፋ የተጠረጠሩ ሰዎችን ጉዳይ የሚመረምረዉ ፖሊስ ምርመራዉን በ11 ቀናት ዉስጥ እንዲያጠናቅቅ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አዘዘ።ዛሬ አዲስ አበባ ያስቻለዉ ፍርድ ቤት የተጠርጣሪ ጠበቆች ባቀረቡት አቤቱታ መሠረት ተጠርጣሪዎች አደረሱት የተባለዉ ጥፋት በተናጥል እንዲቀርብ፣ የተጠርጣሪዎች ሰብአዊ መብት ይዞታ እንዲሻሻልም አዟል።ከ600 በላይ ሠላማዊ ሰዎች በተገደሉበት በማይካድራዉ ጭፍጨፋ ከሚጠረጠሩት ዛሬ ጉዳያቸዉ የታየዉ የ36ቱ ነዉ።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ነጋሽ መሐመድ
ኂሩት መለስ