1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሙኒክ ኦሎምፒክ የሽብር ጥቃት 50ኛ ዓመት መታሰቢያ

ማክሰኞ፣ ነሐሴ 24 2014

በፍዩርሽተንፌልድ ብሩክ ስለሆነው የጀርመን ፖለቲከኞችም ሆኑ ፖሊስ ይቅርታ አልጠየቁም ጉዳዩን የሚያጣራ ኮሚቴም አልተቋቋመም።ስላልተሳካው ጥቃቱን የማክሸፍ ጥረት ማንም ሃላፊነት አልወሰደም። የእስራኤል ልዩ ኃይል አደጋው በደረሰበት ወቅት እርዳታለማድረግ ቢጠይቅም ለምን እንደተከለከለ የተባለ ነገር የለም።

https://p.dw.com/p/4GF0A
Fußball | Länderspiel | Deutschland - England
ምስል Sven Simon/IMAGO

በደቡብ ጀርመንዋ በሙኒክ ከተማ የዛሬ 50 ዓመት በተካሄደው የኦሎምፒክ ጨዋታ ወቅት የተፈጸመው የሽብር ጥቃት ዛሬም ከጀርመናውያን ዐዕምሮ አልጠፋም። 
በደቡብ ጀርመንዋ በሙኒክ ከተማ ፣የኦሎምፒክ ጨዋታ ነሐሴ 21 ቀን 1964 ዓም በተጀመረ በአስራ አንድ ቀኑ በአንድ የኦሎምፒክ መንደር  ድንገተኛ የአሸባሪዎች ጥቃት ደረሰ።በጎርጎሮሳዊው መስከረም 6 ቀን 1972 ምሽት ላይ  በፍልስጤማውያን አሸባሪዎች በተፈጸመው በዚሁ ጥቃት ስምንት እስራኤላውያን አትሌቶችና አንድ ፖሊስ ተገድለዋል። የጥቃቱ 50ኛ ዓመት በጀርመን እየታሰበ ነው። ሀንስ ፎልክል  ከዛሬ 50 ዓመት ወዲህ የሄሊኮፕተር ድምጽ በሰሙ ቁጥር ይረበሻሉ።  ድምጹ ሁሌም ቤል ዩ ኤች አንድ (BELL-UH 1 )የተባሉትን ሁለት ሄሊኮፕተሮች ድምጽ የሰሙበትን በጎርጎሮሳዊው አቆጣጠር መስከረም 6 ቀን 1972ን ያስታውሳቸዋል። ወጣቱ ወታደር ፎልክል በዚያን ለሊት ከባቫርያዋ ግዛት ዋና ከተማ ከሙኒክ ወጣ ብሎ ይገኝ በነበረው የአየር ኃይል ጦር ሰፈር ለአውሮፕላን አብራሪዎች መረጃ የሚተላለፍበት ማማ ውስጥ እየሰሩ ነበር። የስራ ድርሻቸውም አብራሪዎች በጦር ሰፈሩ እንዲያርፉ ማገዝ ነበር። የ21 ዓመቱ ፎልክል ስራ ላይ ሆኖ

München Olympiade 1972 Hubschauber
ምስል AP

ከሙኒክ ከተማ 20 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው የኦሎምፒክ መንደር  ጠዋት የሆነውን በቴሌቪዥን መስኮት ይከታተል ነበር። የዚያን እለት ጠዋት ፍልስጤማውያን አሸባሪዎች፣ የእስራኤል የአትሌቶች ቡድን ማረፊያን ሰብረው በመግባት ክብደት አንሺውን ጆሴፍ ሮማኖንና የነጻ ትግል አሰልጣኝ ሞሼ ዋይንበርግን ገድለው ሌሎች ዘጠኝ እስራኤላውያንን ደግሞ አግተው ነበር።      
የዚያኑ እለት ምሽት 8ቱ አሸባሪዎች ካገቷቸው 9 እስራኤላውያን አትሌቶች  ጋር በሁለት ሄሊኮፕተሮች ተሳፈሩ። አሸባሪዎቹ እሥራኤልና ጀርመን ውስጥ የታሰሩ ጓዶቻቸው እንዲፈቱላቸውም ጠይቀው ነበር ።ግን  አልተሳካላቸውም።የጀርመን ባለሥልጣናት ከአሸባሪዎቹ ጋር ሰዓታት የፈጀ ድርድር ካካሄዱ በኋላ የያኔው የጀርመን የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ሀንስ ዲትሪሽ ጌንሸር አጋቾቹ ወደ ግብጽ ዋና ከተማ ካይሮ እንደሚወሰዱ ቃል ገቡላቸው። ጌንሸር አጋቾቹ በሄሊኮፕተር ከሙኒክ ወጣ ብሎ ወደሚገኘው ሪም አውሮፕላን ማረፊያ እንደሚወስዱና በዚያም የመንገደኞች አውሮፕላን እንደሚጠብቃቸው አረጋገጡላቸው። ይሁንና የጀርመን ፌደራል ድንበር ጠባቂ አብራሪዎች ግን ለአጋቾቹ  ቃል ወደተገባላቸው ካይሮ ሳይሆን እዚያው ሙኒክ ወደሚገኘው ፍዩሪሽተንፌልድብሩክ በተባለው ስፍራ ወዳለ የአየር ኃይል ጦር ሰፈር ወሰዷቸው። ፎልክል ለዶቼቬለ በሰጡት ቃል ምልልስ ዝቅ ብለው ይበሩ የነበሩት አጋቾቹንና ታጋቾቹ የያዙት ሁለቱ ሄሊኮፕተሮች ከቢሮአቸው ፊት ለፊት ከምሽቱ አራት ሰዓት ተኩል ላይ አረፉ። 
የፖሊስ ግብረ ኃይል እቅድ አሸባሪዎቹን ወዲያው ተኩሶ መግደልና ታጋቾቹን ነጻ ማውጣት ነበር።ሆኖም እቅዱ ከሽፎ አጋቾቹ በታጠቁት ክላሺንኮቭ የአጸፋ ጥቃት ሰነዘሩ።በቦታው ድብልቅልቅ ተፈጠረ።ከዚህ ቀደም ታጋቾችን ነጻ የማውጣት ስልጠና ያልወሰዱ የተባሉት ፖሊሶች ርስ በርስ የራድዮ ግንኙነት አልነበራቸውም።በዚህ የተነሳም አንዳንዶቹ ከባልደረቦቻቸው ላይ ሳይቀር ተኩስ እንደተከፈተባቸው ነው የሚነገረው።ፎልክ እንደሚሉት እርሳቸውና ሌሎች በዚያ ይገኙ የነበሩ ወታደሮች አሸባሪዎቹና ታጋቾቹ ወደ ፍዩርሽተንፌልድብሩክ እንደሚመጡ አላወቁም ነበር።  
«እኛ የለሊት ተረኞች ስለነበርን ነው በዚያ መሀል የተገኘነው ።ማንም ስለ ጉዳዩ ምንም ያለን የለም።ተኩስ እስከሚከፈት ድረስ እዚህ ነበርኩ ከዚያ በኋላ ወደዚያ ሄድኩ።»
ተኩስ ሲጀምር ፣ፎልክል  ከቢሮአቸው አቅራቢያ በሚገኝ ክፍል ውስጥ ጥግ ላይ ይገኝ በነበረ ራድየተር ተከለሉ።በቅርብ ርቀት ባልደረባቸው የፖሊስ መኮንን በተባባሪ ጥይት ተመቶ ወደቀ።ሟቹ አንቶን ግላይገርባወር ይባልል።የተኩes ልውውጡ እስከ እኩለ ለሊት ቀጥሎ ፍንዳታ ተከተለ።አንድ አሸባሪ ታጋቾቹ ታስረው ወደተቀመጡበት  አንደኛው ሄሊኮፕተር ቦምብ ወረወረ።ሲነጋ ከፖሊስ መኮንኑ ጋር አምስት አሸባሪዎችም መሞታቸው ተረጋገጠ።ከታጋቾቹ እስራኤሎች መካከልም በሕይወት የተረፈ አነበረም።በማግስቱ የሆነው ፎልክልን አስገርሟል።
«በማግስቱ የኦሎምፒክ ጨዋታው ይቀጥላል ሲባል   ማንም ሊገባው አልቻለም።የተኩስ ልውውጡ ያስከተለee ስብርባሪ እዚያው እንዳለ ነበር።የኦሎምፒክ ጨዋታ ለአንድ ቀን ብቻ ከተቋረጠ በኋላ በማግስቱ ቀጠለ በፍዩርሽተንፌልድ ብሩክ ስለሆነው የጀርመን ፖለቲከኞችም ሆኑ ፖሊስ ይቅርታ አልጠየቁም ጉዳዩን የሚያጣራ ኮሚቴም አልተቋቋመም።ስላልተሳካው ጥቃቱን የማክሸፍ ጥረት ማንም ሃላፊነት አልወሰደም።የእስራኤል ልዩ ኃይል አደጋው በደረሰበት ወቅት እርዳታለማድረግ ቢጠይቅም ለምን እንደተከለከለ የተባለ ነገር የለም።

Terroranschlag auf israelische Sportler im Olympischen Dorf in München
ምስል AP

በሌላ በኩል የጥቃቱ ሰለባ ቤተሰቦች በበኩላቸው ከጥቃቱ ጋር የተያያዙ መረጃዎች የሚገኙባቸውን ሰነዶች ለማየትና ተመጣጣኝ ካሳም እንዲሰጣቸው ለብዙ አሥርት ዓመትታ መታገል ነበረባቸው።ዘንድሮ ደግሞ ቅሬታ ያላቸው ቤተሰቦች በሚቀጥለው ሳምንት በሚካሄደው 50ኛ ዓመት የመታሰቢያ ዝክር ላይ ላለመገኘት አቅደዋል።ሉድቪግ ሽፔንለ በባቫርያ የፀረ ሴማዊነት ኮሚሽነር ናቸው እርሳቸው እንደሚሉት የሰለባዎቹ ቤተሰቦች የዓይን ምስክሮች እና በህይወት የተረፉ የጥቃቱ ሰለባዎች እንደ አስቸጋሪ ድሀ ቤተሰብ ነው የታዩት።ሽፔንለ የዛሬ 50 ዓመት በሙኒክ የሆነውን ለመመርመር ቆርጠው ተነስተዋል።ምዕራብ ጀርመን አሸባሪነትን ማክሸፍ ተስኗታል ሲሉ ይከራከራሉ።ከጥቃቱ በኋላ የሆነውም ለመንግሥት ውድቀት ነው ይላሉ። «ሰዎች ቶሎ ለመርሳት ፈልገው ያን ለማድረግም ብዙ ጥረዋል።ዝምታም መርጠዋል።»ላለፉት አስር ዓመታት ወዲህ እንጂ የተገደሉትን በይፋ ለማስታወስ ከዚያ በፊት የተካሄደ ዝግጅት አልነበረም።ከዛሬ አስር ዓመት ወዲህ  ለምሳሌ በሙኒኩ የኦሎምፒክ ፓርክ መታሰቢያ ይገኛል።
ሀንስ ፎልክል ምንም ሳይቆይ ነበር ወደ መደበኛ ስራው የተመለሰው ስራ ሲጀምርም በቦምብ እንዳልነበረ የሆነው ሄሊኮፕተር ስብርባሪ እንኳን አልተነሳም  ነበር። ያኔ ምንም ዓይነት የስነ ልቦና ምክርም አላገኑኙም።የሙኒኩ ኦሎምፒክ ጀርመን ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ መልካም ገጽታዋን እንድታሳይበት ታስቦ የተካሄደ ነበር።የሙኒኩ ኦሎምፒክ ሰላም የሚከበርበት እንዲሆንም ነበር የታቀደው ። ከሙኒኩ ኦሎምፒክ ከ36 ዓመታት በፊት በናዚ ጀርመን አስተዳደር በርሊን ውስጥ  የኦሎምፒክ ጨዋታ ተካሂዶ ነበር። የሙኒኩ ኦሎምፒክ አይሁዶች የተፈጁበት የሁለተኛው የዓለም ጦርነት ባበቃ በ27 ነበር የተካሄደው።በጦርነቱ ከስድስት ሚሊዮን በላይ አይሁዶች እንደተገደሉ ይገመታል። በሙኒኩ ኦሎምፒክ ወቅትም በጀርመን ምድር በአሸባሪዎች ሕይወታቸው ያለፈው አይሁዶች ነበሩ።የጀርመን መንግሥት ደግሞ በወቅቱ ጥቃቱን ሊከላከልላቸው አልቻለም ተብሏል።አና ኡልሪክ ቤርግሃይም የፍሪሽተን ፌልድ ብሩክ ታሪካዊ ማኅበር ሊቀመንበር ናቸው።ላለፉት 50 ዓመታት ጉዳዩ  ለምን ትኩረት እንዳልተሰጠው ይገረማሉ።« ለ50 ዓመታት ባለስልጣናት ጥቃቱ በደረሰበት ምሽት ስለነበሩት የፖሊስ መኮንኖች ተneቀው አያውቁም።ጉዳት የደረሰባቸውን  የአየር ኃይል አባላት የእሳት አደጋ መከላከያ ሠራተኞች ባለፉት  50 ዓመታት ተጠይቀው አያውቁም። እናም ስለዚህ አደጋ ምን ሊሰማቸው ይችላል።? »
ፎልክል ዛሬ በጎርጎሮሳዊው መስከረም 6 ቀን 1972 ዓም ስለሆነው በይፋ በይፋ መናገር ጀምረዋል።የሰለባዎቹን ቤተሰቦች እስካሁን አግኝተው አያውቁም። ይህ አስበውትም አያውቁም። ፍርሀት አላቸው።በርሳቸው እምነትምንም እንኳን አደጋው 50 ዓመት ቢሆነውም አሁንም ብዙ መባል ያለበት ነገር እንዳለ ይሰማቸዋል።

Gedenken an das Attentat auf israelische Sportler vor 30 Jahren, Kranzniederlegung Nähe des Münchener Olympiadorfes
ምስል AP

ኂሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ