መኢአድ በሰሞኑ የመንግሥት እርምጃ ላይ
ዓርብ፣ ኅዳር 7 2011ማስታወቂያ
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ መንግሥት መውሰድ የጀመረው የህግ የበላይነትን የማረጋገጥ እርምጃ በጎ ጅምር ነው ሲል የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት መኢአድ አወደሰ። መኢአድ ዛሬ በጽህፈት ቤቱ በሰጠው መግለጫ መንግሥት ሰሞኑን በሙስናና እና በሰብዓዊ መብት ጥሰት ጠርጥሮ የያዛቸውን የቀድሞ ከፍተኛ ባለሥልጣናትን ለህግ ማቅረብ መጀመሩ ተጠናክሮ መቀጠል አለበትም ብሏል። ለመንግስት እርምጃ ተግባራዊነትም የአፍሪቃ ህብረት እና የተመድ እንዲሁም ጎረቤት ሀገራትም እገዛ እንዲያደርጉ ጠይቋል። በዚሁ ጋዜጣዊ መግለጫው ላይ ድርጅቱ በተለያዩ አካባቢዎች ስላካሄዳቸው እንቅስቃሴዎች እና ስለ ከፈታቸው አዳዲስ ቢሮዎችም ገለጻ አድርጓል። መግለጫውን የተከታተለው የአዲስ አበባው ወኪላችን ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ