የመቐለ ተሰብሳቢዎች መድረክ
ሐሙስ፣ ኅዳር 25 2012ማስታወቂያ
የትግራይ ክልላዊ መንግስት መቐለ ላይ የሰበሰባቸዉ የኢትዮጵያ መንግስት ተቃዋሚ ፓርቲ ተወካዮች የኢትዮጵያ ፌደራሊስት ኃይላት መድረክ ያሉትን ስመመስረታቸዉን አስታወቁ።ለሁለት ቀን የተነጋገረዉን ስብሰባ በንግግር የከፈቱትና የዘጉት የትግራይ ምክትል ርዕሠ-መስተዳድርና የሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ሊቀመንበር ዶክተር ደብረ-ፅዮን ገብረ ሚካኤል ለተሰብሳቢዎቹ እንደነገሩት ተሰብሳቢዎቹ የሕወሓት ተላላኪዎች አይደሉም።በስብሰባዉ ላይ 50 የሚደርሱ የፖለቲካ ፓርቲዎችን የወከሉ ፖለቲከኞች መሳተፋቸዉ ተነግሯል።እዚያዉ ትግራይ ዉስጥ የሚንቀሳቀሰዉ አረና ትግራይ ግን በስብሰባዉ አልተሳተፈም።
ሚሊዮን ኃይለስላሴ
ነጋሽ መሐመድ
ኂሩት መለሰ