የመቀሌ ነዋሪዎች አስተያየት
ሐሙስ፣ ሰኔ 20 2011ማስታወቂያ
በወቅቱ ለቀብር የወጡት እጅግ በርካታ ወጣቶች የተለያዩ መፈክሮች ሲያሰሙ፤ በሌላ በኩል ደግሞ ለቀብር በስፍራው የተገኙት የትግራይ ዴሞክራሲያ ትብብር ሊቀመንበር ዶክተር አረጋዊ በርሄም ችግር አጋጥሟቸው እንደነበር ተሰምቷል። በትግራይ የፀጥታ ኃይሎች ታስረዋል የተባለላቸው ከህወሀት አንጋፋ መስራቾች አንዱ የነበሩት ዶክተር አረጋዊ ዛሬ አለመታሰራቸውን ለሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን የገለፁ ሲሆን፤ በጉዳዩ ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ ለመስጠት ዝግጅት ላይ መሆናቸውን ለመረዳት ችለናል። የትናንቱን የመቀሌ ክስተት ያካተተው የዘጋቢያችን ሚሊዮን ኃይለ ሥላሴ ዝርዝር ዘገባ እነሆ።
ሚሊዮን ኃይለ ሥላሴ
ሸዋዬ ለገሠ
ነጋሽ መሐመድ