የሕዝብ እና ቤት ቆጠራ መራዘም
ሐሙስ፣ መጋቢት 19 2011ማስታወቂያ
በተደጋጋሚ እየተራዘመ መካሄድ ከነበረበት ግዜ ሁለት ዓመት ያለፈው የሕዝብና ቤት ቆጠራ በያዝነው ወር መጋቢት 29 ሊካሄድ ዕቅድ ወጥቶለት በዝግጅት ሂደት ላይ ከቆየ በኋላ ባሳለፍነው ሳምንት ላልተወሰነ ግዜ እንዲተላለፍ የውሳኔ ሀሳብ ቀርቧል። በጉዳዩ ላይ የተለያዩ አስተያየቶች እየቀረቡ ሲሆን የትግራይ ክልል መንግሥት የአስፈፃሚውን አካል ውሳኔ ተቃውሞታል። የሕዝብና ቤት ቆጠራን አስመልክቶ የተላለፈውን የውሳኔ ሀሳብ መግለጫ የሰጡት የትግራይ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድርና የንግድ፣ ኢንዳስትሪና ከተማ ልማት ቢሮ ሐላፊ ዶክተር አብረሃም ተኸስተ ቆጠራው አለመካሄዱ የመንግሥትን የማስፈፀም አቅም ጥያቄ ውስጥ የሚከት ነው ብለዋል። እንዲሁም በሂደቱም የግልፅነት ችግር መኖሩን አክለው ገልፀዋል።በትግራይ ክልል በኩል ግን ቆጠራውን ለማካሄድ ሙሉ ዝግጁነት መኖሩን ዶክተር አብርሃም ተኸስተ ተናግረዋል፡፡ ይህን አስመልክቶ የሚመለከታቸው የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች ለማነጋገር ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።
ሚሊዮን ኃይለ ሥላሴ
ሸዋዬ ለገሠ
ኂሩት መለሰ