የሐርር እና የድሬዳዋ የዛሬ ውሎ
ረቡዕ፣ ሰኔ 24 2012ማስታወቂያ
ሐረር ከትናንት ዛሬ አንጻራዊ ጸጥታ የሰፈነባትም ቢሆንም ዛሬም የከተማዋ የተለመደ እንቅስቃሴ የለም። የትራንስፖርት አገልግሎት እንዳልተጀመረ ነዋሪዎች ለዶቼቬለ ተናግረዋል።የመከላከያ ኃይልና ፖሊስ ትናንት ጥፋት የተፈጸመባቸውን አካባቢዎች እየጠበቁ ነው።በድሬዳዋ ደግሞ ለገሃሬ በተባለው አካባቢ ተቃውሞ ና ከፀጥታ ኃይሎች ጋር ግጭቶች እንደነበሩ የዓይን እማኞች ተናግረዋል።ስለ ዛሬው የድሬዳዋና የሐረር ውሎ የድሬዳዋው ወኪላችን መሳይ ተክሉ ከዓይን እማኞች ያገኘውን መረጃ አካፍሎናል።
መሳይ ተክሉ
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ