የሐረር ቢራ ሠራተኞች የረሀብ አድማ
ሰኞ፣ ግንቦት 5 2005ማስታወቂያ
ቁጥራቸው ወደ 80 የሚጠጋ የሐረር ቢራ የጥበቃ ሠራተኞች የረሀብ አድማ አደረጉ። የኅብረት ስምምነቱ የአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ እንዲሁም የፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ ስምምነትን በጣሰ መልኩ ድንገት ከስራ ስላባረረን ከቤተሰቦቻችን ጋር ለችጋር ተዳርገናል ሲሉ ሠራተኞቹ አማረዋል። ሠራተኞቹ ለአንድ ቀን በግቢው ውስጥ የረሀብ አድማ ቢያደርጉም ከሌሊቱ 6 ሠዓት ላይ በፖሊስ ኃይል እንዲወጡ ተደርገዋል። የሰራተኞቹ ማኅበር በበኩሉ ይህ ሕገወጥ ድርጊት እስካልተቀለበሰ ድረስ ወደ ቀጣይ ርምጃ እንሸጋገራለን ሲል ዝቷል። ከአዲስ አበባ ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር ዝርዝሩን ልኮልናል።
ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር
ማንተጋፍቶት ስለሺ
አርያም ተክሌ