Hirut Melesseሐሙስ፣ ሰኔ 20 2016የዜና መጽሔት ዝግጅታችን
ኢትዮጵያ ወታደሮቿ ድንበር አቋርጠዋል የሚለውን የሶማሊያን ውንጀላ ማስተባበሏን፤ በአማራ ክልል በባህር ዳር ከተማ በተካሄደው ኮንፈረንስ ተሳታፊዎች በክልሉ ከሚካሄደው ግጭት ጋር በተያያዘ መንግስት በቁጥጥር ስር የዋላቸውን እንዲፈታ መጠየቃቸው፤በምዕራብ ኦሮሚያ ክልል የመንግስት የፀጥታ ኃይሎች ነዋሪዎችን በጅምላ እያሰሩ ነው መባሉ፤የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር በክልሉ ሕግ ማስከበር አልቻለም ሲሉ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የተቃዋሚ ፓርቲዎች መተቸታቸው በአሜሪካ የሚገኙ ሰባት የኢትዮጵያ ሲቪል ድርጅቶች አዲስ ህገ መንግስት አስፈላጊነትን ላይ መግለጫ መስጠታቸውን ከሚያስቃኘን ግጅቶች መካከል ናቸው።