የሆድ ህመም እና መንስኤዎቹ
ማክሰኞ፣ ጥር 10 2008ማስታወቂያ
ከአድማጮች ለሚቀርቡ ጤናነክ ጥያቄዎች ማብራሪያ ለመስጠት የሁልጊዜም ተባባሪያችን የሆኑት የዉስጥ ደዌ እና ከኢንፌክሽን ጋር የተያያዙ በሽታዎች ላይ ለረዥም ጊዜ የሠሩት ዶክተር ቶሌራ ወልደየስ፤ ለሆድ ህመም የሚዳርጉ ባክቴሪያዎች ዓይነታቸዉ ይለያያል ይላሉ። የህመሙ ምክንያቶች አሜባም ሆነ ጃርድያ ያሉ ጥገኛ ተሐዋሲያን ሊሆኑ ይችላሉ። ይህ ሁሉ ህመምተኛዉ ሀኪም ጋር ቀርቦ በሚደረግለት ምርመራ ነዉ ምንነቱ ሊጣራ የሚችለዉ። ጥያቄያቸዉን የላኩልን አድማጭ ከማብራሪያዉ እንደሚጠቀሙ ተስፋ እናደርጋለን፤ ሌሎቻችሁም ጤናነክ ጥያቄዎቻችሁን መላክ ትችላላችሁ፤ የሚመለከታቸዉን ሃኪሞች በእናንተ ስም እንጠይቃለን። ማብራሪያዉን ከድምፅ ዘገባዉ ያድምጡ
ሸዋዬ ለገሠ
አዜብ ታደሰ