የሁዳዴ ጾም
ኢትዮጵያ ሀይማኖተኛ ከሚባሉት ሀገራት መካከል አንዷ ናት። ለኦርቶዶክስ እና ለካቶሊክ እምነት ተከታዮች ወቅቱ የጾም ጊዜ ሲሆን፣ የፖለቲካ ችግር የሚታይባት የዚችው ሀገር ህዝብ ከማንኛውም ጊዜ ይበልጥ በአሁኑ ወቅት ጊዜውን በፀሎት ያሳልፋል።
ሰባት የተለያዩ የጾም ጊዚያት
በዓቢይ ጾም ወቅት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች 55 ቀናት፣ ካቶሊኮች ደግሞ 40 ቀናት ይጾማሉ። በኦርቶዶክስ እምነት በዓመት ሰባት የተለያዩ የጾም ጊዚያት አሉ። የእምነቱ ተከታዮች በዓመት ከ165 እስከ 250 ቀናት ይጾማሉ።
ጠንካራ የአጿጿም ሕጎች
በአንድ የጎንደር ቤተ ክርስትያን የእምነቱ ተከታዮች ግንባራቸው ላይ በአመድ የመሥቀል ምልክት ይሰራሉ። በጾም ወቅትም ወተት እና እንቁላልን የመሳሰሉ የእንሰሳ ተዋፅዖዎችን አይበሉም። ከዚህ በተጨማሪ እስከ ዘጠኝ ሰዓት ከቀትር በኋላ ድረስ አይበሉም፣ አይጠጡም።
እምነት እና መንፈሳዊነት
ለኢትዮጵያውያን ጾም እና የአጿጿም ዘዴ በምዕራቡ ዓለም ብዙዎች ሊረዱት የማይችሉት መንፈሳዊ ትርጓሜ አለው። የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ዲያቆን መኮንን እንደሚሉት፣ በስነ መለኮት አስተምህሮት መሰረት፣ ወደ እግዚአብሔር ለመቅረብ ጾም ፣ ማለትም ከስጋዊ ፍላጎቶች መራቅ አስፈላጊ ነው።
ከአንድ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ የሚጠበቁ ነገሮች
የቤተ ክርስትያን ቀነኖ በጾም ወቅት የአልክሆል መጠጥ እና ወሲባዊ ግንኙነትን ባይከለክልም፣ እንደ ዲያቆን መኮንን ገለጻ፣ ብዙ ምዕመናን በፈቃዳቸው ከነዚህ ተግባራት ይቆጠባሉ።
ሀይማኖታዊነት በኢትዮጵያ
እጎአ በ2015 ዓም የ«ፒው» ምርምር ማዕከል ያየጣው አንድ ጥናት እንደሚያሳየው፣ ከኢትዮጵያ ህዝብ መካከል 98% ሀይማኖትን የማንነቱ መገለጫ አድርጎ ይመለከተዋል።
የሀይማኖት ምልክቶች
ብዙ ኢትዮጵያውያን አንገታቸው ላይ መሥቀል ያደርጋሉ። የማርያምን እና የኢየሱስ ክርስቶስን ስዕሎች፣ እንዲሁም፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን በብዙ ታክሲዎች እና ሚኒባሶች መስታወቶች ላይ ይለጥፋሉ። በመኖሪያ ቤታቸውም እነዚህን ስዕሎች እና ጥቅሶች ይሰቅላሉ።
«ስክሪንሴቨርስ»
ከእምነታቸው ጋር የተገናኙ ስዕሎች በብዙዎች የእጅ ስልኮች ላይ ይታያሉ።
የቀኑ ጾም አፈታት
ጿሚዎች የቀኑን ጾም ከአትክልት እና ከጥራጥሬ በተሰሩ የተለያዩ ምግቦች ይፈታሉ።
ዕለታዊው ፀሎት
ምዕመናኑ የጾሙ ጊዜ ካበቃ በኋላም ፀሎታቸውን አያቋርጡምም፣ በተለይ፣ በችግር ጊዜ። ጄምስ ጄፍሪ/አርያም ተክሌ