የሁለቱ የእግር ኳስ ተጫዋቾች የነገ ህልም
ዓርብ፣ ሰኔ 13 2006ማስታወቂያ
የዛሬዎቹ የወጣቶች ዝግጅት እንግዶቻችን የእግር ኳስ ጨዋታውን የሚመለከቱት ከአብዛኞቻችን ለየት ባለ መልኩ ነው። ፍረ እግዚ መንግሥቱ እና ጋቶች ፋኖም ይባላሉ። አንዱ አቅዶ ሌላኛው እንደቀልድ ነው የእግር ኳስ ተጫዋች የሆኑት። ዛሬ ሁለቱም የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ተጫዋቾች ናቸው።
የ21 ዓመቱ ፍረ እግዚ የሞጆ ልጅ ነው። ወደ አዲስ አበባ ከመሄዱ በፊት ድሬ ድዋ ላይ በተካሄደ ውድድር ተካፍሎ በመጀመሪያ «ተስፋ» የሚባል ቡድን ገባ ።ከዛም ስድስት ወር ባልሞላ ጎዜ ባሳየው ጥሩ ውጤት የተነሳ የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብን እንደተቀላቀለ ይናገራል። በ 2003 ዓ ም ማለት ነው።
ከፍረ እግዚ ጋር አብሮ የሚጫወተው የ23 ዓመቱ ጋቶች ደግሞ ጋምቤላ ውስጥ ነው ተወልዶ ያደገው። ኳስ መጫወት የጀመረው የግድ ኳስ ተጫዋች እሆናለሁ በሚል አልነበረም። በኋላ ግን በክልል ባደረገው ውድድር ወደ አዲስ አበባ ሄዶ ለቡና ክለብ ለመጫወት እድል አገኘ።
የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ የእግር ኳስ ተጫዋቾች ፍረ እግዚ መንግሥቱ እና ጋቶች ፋኖም ሌላም ስለ ራሳቸው እና በብራዚል ስለሚካሄደው የአለም ዋንጫ ያሉን አለ። ከድምፅ ዘገባው ተከታተሉት።
ልደት አበበ
ሂሩት መለሰ