1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች

ረቡዕ፣ ሚያዝያ 25 2015

የሀረሪ ወጣት ሴቶች እጅግ አምረው እና ተውበው የሚታዩበት ዓመታዊው የሸዋል ዒድ በዓል ሰሞኑን በደመቀ መልኩ ተከብሯል። አስተያየታቸውን ያካፈሉን የበዓሉ ታዳሚ ወጣት ሴቶች በዓሉ በእጅጉ የተለየ ትርጉም እንደሚሰጣቸው ተናግረዋል።

https://p.dw.com/p/4QpwY

በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ የረመዳን ፆም ወቅት ማጠናቀቂያ ላይ ከሚከበረው የኢድ አልፈጥር በኃላ ያሉ ስድስት ተጨማሪ የፆም ቀናት በኃላ በሀረሪ ክልል ማህበረሰብ ዘንድ በሚከበረው የሸዋል ኢድ በተለየ መልኩ በባህላዊ አልባሳት የተዋቡ የሀረሪ ወጣት ሴቶች ለበዓሉ ድምቀት ሆነው ያመሻሉ።
በጥንታዊቷ ሀረር ከተማ በሚገኘው የጀጎል ግንብ በሚካሄደው የበዓሉ የምሽት ድግስ ከተለመዱ ኩነቶች አንዱ መተጫጨት መሆኑን ወጣቶቹ ለዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች ዝግጅታችን ገልፀዋል። ምንም እንኳን እነሱ መሰል ታሪክ ባይኖራቸውም የቆየ እና የሚቀበሉት ባህል መሆኑንም አጫውተውናል።በጉጉት የሚጠብቁት የሸዋል ዒድ በዓል ደርሶ ደምቆ ለመታደም ዝግጅት እንደሚያደርጉም ወጣቶቹ ነግረውናል። የሀረሪ ወጣቶች ይህ ባህላቸው ይበልጥ እንዲያድግ እና ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፍ የበኩላቸውን እንደሚወጡም ጠቁመዋል።  #ዝምታሰባሪአዳጊሴቶች #GirlzOffMute


ዘገባ: ሊዲያ መለስ
ቪዲዮ: መሳይ ተክሉ