1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች: ስካውት ናርዶስ እና ጥበቧ

ረቡዕ፣ የካቲት 30 2014

በሀዋሳ ከተማ ነዋሪ የሆኑት ታዳጊ ናርዶስ ታደለ እና ጥበቧ ወልዴ በከተማው የሚገኘውን ቡናማ ስካውት ማህበር በመቀላቀል ማህበራዊ ተሳትፎ እያደረጉ እንደሚገኙ ይናገራሉ፡፡

https://p.dw.com/p/48DIp

ቀደምሲል ሥለ በጎነት ፣ ሥለ አገር ፍቅር እና ሥለ ሠንደቅ ዓላማ ክብር ያላቸው እውቀት ዝቅተኛ አንደነበር የሚናገሩት ታዳጊዎቹ የስካውት ማህበሩን ከተቀላቀሉ በኋላ ግን የተሻለ ግንዛቤ አግኝተናል ይላሉ፡፡ የስካውት እንቅስቃሴ ለመጀመሪያ ጊዜ  እጎአ በ 1907 በታላቋ ብሪታንያ የተጀመረ ሲሆን ከዚያን ጊዜ አንስቶ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከ300 ሚሊዮን በላይ ህፃናት እና ወጣቶች የዚህ እንቅስቃሴ አካል ለመሆን ችለዋል። 

ዘገባ ፡- ሊሻን ዳኜ
ቪዲዮ ፡- ሸዋንግዛው ወጋየሁ