ዚምባቡዌ፤ ሙጋቤና የኮሌራ ወረርሽኝ13 ታኅሣሥ 2001ሰኞ፣ ታኅሣሥ 13 2001በዚምባቡዌ የሚታየዉ የምጣኔ ሃብት ቀዉስና የኮሌራ ወረርሽኝ በእሳቸዉ ምክንያት ሳይሆን በቀድሞ ቅኝ ገዢ ብሪታኒያ መዘዝ የተከሰተ መሆኑን ፕሬዝደንት ሮበርት ሙጋቤ ገለጡ።https://p.dw.com/p/GLPr...የተገኘዉ ይጠጣልምስል APማስታወቂያየአገሪቱ ገዢ ፓርቲ ዛኑ ፒኤፍ ባለፈዉ ያካሄደዉን ዓመታዊ ጉባኤ ቅዳሜ ዕለት ሲያጠናቅቅ ይህን መሰሉን መልዕክት ያስተላለፉት ሙጋቤ እግረ መንገዳቸዉንም ከስልጣን የመዉረድ ሃሳብ እንደሌላቸዉ አመላክተዋል። በአገሪቱ የተከሰተዉ የኮሌራ ወረርሽኝ ብዙዎችን እየገደለ ባለበት በዚህ ወቅት ሙጋቤ ከእሱ ይልቅ ትኩረታቸዉን የጋለዉ የፖለቲካ ዉጥንቅጥ ላይ ማድረጋቸዉ አስተችቷቸዋል።