ዘ ሄግ፤ ICC ዣን ፒየር ቤምባ ላይ የ18 ዓመት እሥራት ፈረደ
ማክሰኞ፣ ሰኔ 14 2008ማስታወቂያ
የ53 ዓመቱ ዣን ፒየር ቤምባ ባለፈዉ መጋቢት ወር ነበር በቀረቡባቸዉ አምስት የጦር ወንጀል እና በሰብዓዊ ነት ላይ የተፈጸሙ ወንጀሎችን የሚጠቅሱ የክስ ጭብጦች ጥፋተኛ የተባሉት። የኮንጎ ነፃ አዉጭ ንቅናቄ የተሰኘ የግላቸዉ ጦር እንዳላቸዉ የሚነገረዉ ቤምባ፤ ከጎርጎሪዮሳዊዉ 2002 እስከ 2003ዓ,ም ድረስ ይህን ጦር ወደ ማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፑብሊክ በመላክ መፈንቅለ መንግሥት ለማድረግ ሞክረዋል የሚል ክስም ቀርቦባቸዋል። የICC አቃቢያነ ሕግ በተለይ አስገድዶ መድፈርን እንደጦር ስልት እንዲጠቀሙ አድርገዋል በማለት ክስ የመሠረቱባቸዉ ቤምባ ቢያንስ 25ዓመት እንዲፈረድባቸዉ ነበር የጠየቁት። ሆኖም የፍርድ ቤቱ ዳኛ ሲልቪያ ሽታይነር ቤምባ አስገድዶ መድፈርን ጨምሮ ፣ የጭካኔ ግድያ እና ርህራሄ የራቀዉ ዘረፋ የፈጸመ ጦራቸዉን መቆጣጠር እንዳልቻሉ በመጥቀስ በአጠቃላይ ፍርድ ቤቱ 18 ዓመት እንደፈረደባቸዉ ገልጸዋል።
ሸዋዬ ለገሠ
አዜብ ታደሰ