1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ተመረቀ

እሑድ፣ የካቲት 3 2016

"ዓድዋ ዜሮ ዜሮ" በሚል ስያሜ ከ ሐምሌ 2011 ዓ. ም ጀምሮ ላለፉት አራት ዓመታት ሲገነባ የቆየው የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ርእሠ ብሔር ሣኅለ ወርቅ ዘውዴ ፣ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት በተገኙበት ዛሬ እሑድ ተመርቋል።

https://p.dw.com/p/4cH07
Äthiopien | Adwa Victory Museum
ምስል Addis Ababa city communication office

የአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም በታላቅ ድምቀት ተመርቋል

የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ተመረቀ

መሃል አዲስ አበባ ፒያሳ ላይ የተገነባው የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ዛሬ የካቲት 3 ቀን 2016 ዓ.ም ተመረቀ። 

"ዓድዋ ዜሮ ዜሮ" በሚል ስያሜ ከ ሐምሌ 2011 ዓ. ም ጀምሮ ላለፉት አራት ዓመታት ሲገነባ የቆየው የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ርእሠ ብሔር ሣኅለ ወርቅ ዘውዴ ፣ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት በተገኙበት ዛሬ እሑድ ተመርቋል።

የዓድዋ ድል መታሰብያ ሙዚየም ኢትዮጵያውያን ከ 128 ዓመታት በፊት ለቅኝ ግዛት የመጣውን የጣልያን ወራሪ ኃይል በአንድነት መክተውና አሸንፈው ነፃነታቸውን ያስከበሩበት እና ለጥቁር ሕዝቦች ሁሉ የነፃነት ምልክት መሆን ያስቻሉ የድሉ መሪዎች፣ የጦርነቱ ተሳታፊዎች እና ሌሎች ታሪካዊ እውነታዎች በአንድ ላይ የተገለጡበት ነው ተብሏል።

የአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም
ዓድዋ ድል መታሰብያ ሙዚየም ኢትዮጵያውያን ከ 128 ዓመታት በፊት ለቅኝ ግዛት የመጣውን የጣልያን ወራሪ ኃይል በአንድነት መክተውና አሸንፈው ነፃነታቸውን ያስከበሩበት እና ለጥቁር ሕዝቦች ሁሉ የነፃነት ምልክት መሆን ያስቻሉ የድሉ መሪዎች፣ የጦርነቱ ተሳታፊዎች እና ሌሎች ታሪካዊ እውነታዎች በአንድ ላይ የተገለጡበት ነው ተብሏል።ምስል Addis Ababa city communication office

የመታሰቢያ ሙዚየሙ ምን ይዟል?

አድዋ ዜሮ ዜሮ በሚል ስያማ የተገነባው የድሉ መታሰቢያ ሙዚየም ስያሜው የአዲስ አበባ ከተማም ይሁን የኢትዮጵያ አማካይ ሥፍራ "መነሻ" መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በጉብኝቱ ወቅት ለርእሠ ብሔር ሣኅለወርቅ ዘውዴ ሲያስረዱ ተደምጠዋል።አድዋ እንዴት ይዘከር?

ከዳግማዊ ዐፄ ምኒልክ ሃውልት ፣ ከአራዳ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስትያን፣ ከአዲስ አበባ ከተማ መሥተዳድር መሥሪያ ቤት በሚያዋስነው የፒያሳ እምብርት ላይ በታነፀው ይህ የዐድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ውስጥ የጦርነቱን መሪዎች ዳግማዊ ዐፄ ምኒልክን፣ የንግሥተ ነገሥት ጣይቱን ጨምሮ  የዋና ዋናውቹ የጦር መሪዎች ሃውልቶች ተቀርጸው ቆመውላቸዋል። ፈረሶች ፣ ጦርና ጋሻዎች፣ ልዩ ልዩ ታሪካዊ ቁሶች እና ተምሳሌቶችም በሙዚየሙ ውስጥ ተቀምጠዋል።

ይህ የድል መታሰቢያ ሙዚየም ድሉ ለአፍሪካዊያንም ይሁን ለጥቁር ሕዝቦች ሁሉ ያበረከተው ለነፃነት የመነሳሳት ስንቅ ፣ ታላላቅ መሪዎች ስለ ድሉ የተናገሩትን ጭምር አካትቶ የያዘ መሆኑ ለየት ባለ አቀራረብ በተዘጋጀው የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ጉብኝት እና የጋዜጠኞች ማስጎብኘት ሥነ ሥርዓት ላይ ተገልጿል።

የዐድዋ ድል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ክብር ማሳያ፣ የጥቁር ሕዝቦች የነፃነት ተጋድሎ ፋኖስ መሆኑ ይነገርለታል። 

የአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም
ይህ የድል መታሰቢያ ሙዚየም ድሉ ለአፍሪካዊያንም ይሁን ለጥቁር ሕዝቦች ሁሉ ያበረከተው ለነፃነት የመነሳሳት ስንቅ ፣ ታላላቅ መሪዎች ስለ ድሉ የተናገሩትን ጭምር አካትቶ የያዘ መሆኑ ለየት ባለ አቀራረብ በተዘጋጀው የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ጉብኝት እና የጋዜጠኞች ማስጎብኘት ሥነ ሥርዓት ላይ ተገልጿል።ምስል Addis Ababa city communication office

በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ጉብኝት እያደረጉ ያሉት ርእሠ ብሔር ሣኅለወርቅ ዘውዴም ሆነ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገና ንግግር ያደረጉ ባለመሆኑ ለሙዚየሙ ግንባታ የወጣው ወጪ ምን ያህል እንደሆነ ፣ ስለ ሀገራዊ ፋይዳው ያደርጉታል ተብሎ የሚጠበቀውን ንግግር በዚህ ዘገባ

ማካተት አልቻልንም።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ባለፈው ሳምንት ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ ይህንን ብለው ነበር።የአድዋ ድልን አከባበር አድማስ ለማስፋት ያቀደው መድረክ

"ዐድዋ ጀመርን። ገና ነው። የጀመርነውን ይዘን ጥረት እያደረግን ከሄድን በሀገር ደረጃ ከፍተኛ ለውጥ ማምጣት ይቻላል" 

በዚህ የምረቃ ሥነ ሥርዓት ላይ ዶቼ ቬለን ጨምሮ ሌሎች የውጭ መገናኛ ብዙኃንም የተጋበዙ ባለመሆኑ በሥፍራው ተገኝተን መዘገብ አልቻልንም። 

128 ኛው የዓድዋ ድል ብሔራዊ ክብረ በዓል ከሦስት ሳምንታት በኋላ የካቲት 26 ቀን 2016 ዓ.ም ይከበራል።

ሰለሞን ሙጬ

ታምራት ዲንሳ