የኢትዮጵያዉ ጠቅላይ ሚንስትር ለኖቤል
ረቡዕ፣ ነሐሴ 2 2010ማስታወቂያ
የኢትዮጵያዉ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ ለታላቁ የዓለም የሠላም ሽልማት ለኖቤል እንዲታጩ ሁለት የዉጪ ፖለቲከኞች ድጋፍ መስጠታቸዉን አስታወቁ። የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲ ግንባር (ኢሕአዴግ) ሥልጣን እንዲይዝ ከፍተኛ ድጋፍ ሰጥተዋል የሚባሉት የቀድሞዉ የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪቃ ጉዳይ ረዳት ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ኸርማን ኮሕን እንደሚሉት ዶክተር አብይ ለጀመሩት የአንድነት እና የዴሞክራሲ መርሕ ኖቦል ቢሸለሙ ይደግፋሉ። የስዊድን የምክር ቤት እንደራሴ አንድረሽ ኦስተንበርግ በበኩላቸዉ ዶክተር ዐብይ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለአካባቢዉም ሠላም የሚጠቅም እርምጃ እየወሰዱ ነዉ። የፍራንክፍረቱ ወኪላችን እንዳልካቸዉ ፍቃደ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።
እንዳልካቸዉ ፈቃደ
ነጋሽ መሐመድ
አርያም ተክሌ