ወደ አፋር የተዛመተው የትግራይ ጦርነት እና ያሳደረው ተጽዕኖ
ዓርብ፣ ጥቅምት 12 2014ማስታወቂያ
ከጥቅምት 01 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀመሮ በአዲስ መልክ ያገረሸውን የትግራዩ ጦርነት ተከትሎ በአፋር ክልል በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች መፈናቃላቸውን ክልሉ አስታወቀ፡፡
አስተያየታቸውን ለዶይቼ ቬለ የሰጡት የክልሉ ባለስልጣናት በአፋር እና ትግራይ አዋሳኝ አከባቢ በሚገኙ የአፋር ዞን 2 እና ዞን 4 በሚገኙ ወረዳዎች ለተፈናቀሉ የድጋፍ ቁሳቁስ ማድረስም ፈታኝ ሆኗል ብለዋል፡፡ በክልሉ በአዋሳኝ አከባቢ በሚገኙ ጭፍራ፣ በርሃሌ እና መጋሎ ወረዳዎች አሁን ላይ የጦርነት ቀጠና መሆናቸውንም ባለስልጣናቱ አክለው ገልጸዋል፡፡
የአዲስ አበባ ዘጋቢያችን ስዩም ጌቱ በዚህ ላይ ዝርዝር ዘገባ ይዟል፡፡
ሥዩም ጌቱ
ታምራት ዲንሳ
ነጋሽ መሐመድ