ኮሮና ለመከላከል የመገናኛ ብዙሀን ሚና
ሐሙስ፣ ሚያዝያ 1 2012ማስታወቂያ
የኮሮና ተህዋሲ ወረርሽኝን ለመከላከል መገናኛ ብዙሃን ህዝብን በማስተማር ረገድ መልካም የሚባል ስራ ላይ መሆናቸውን ዶቼ ቬለ ያነጋገራቸው ሰዎች ተናገሩ። በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ስለ ኮሮና ቫይረስ ሰፊ ሽፋን እንደሚሰጡ አነቃቂም አስጠንቃቂም መልዕክቶች አሁንም አሁንም በስፋት ለህዝብ እያደረሱ መሆኑን አስተያየት ሰጭዎቹ ተናግረዋል።ጊዜው የመገናኛ ብዙሃኑ ዋጋና ኃይላቸው ከፍ ያለበት ነው ያሉት አንድ የጋዜጠኝነት መምህር ደግሞ፣ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች በጉዳዩ ላይ ያላቸው ግንዛቤ ውሱን በመሆኑ ራሳቸውን ከህዝቡ አንድ እርምጃ ማስቀደም ይኖርባቸዋል ሲሉም አሳስበዋል። ሰሎሞን ሙጬ ከአዲስ አበባ ተጨማሪ ዘገባ አሰናድቷል።
ሰሎሞን ሙጬ
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ