1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኬንያ በፀጥታዉ ም/ቤት የተለዋጭ አባልነት መቀመጫ አገኘች

ዓርብ፣ ሰኔ 12 2012

ኬንያ በአብላጫ ድምፅ የተመድ የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት የተለዋጭ አባልነት መቀመጫ አገኘች። ትናንት ምሽት ኒዮርክ ውስጥ በተከፈተው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ በተካሄደው የድምጽ አሰጣጥ ስርዓት ላይ ኬንያ እና  ጅቡቲ ከምስራቅ አፍሪቃ ሃገራት የቀረቡ እጩ ሃገራት ነበሩ።

https://p.dw.com/p/3e3vH
Sicherheitsrat der UN berät Erhaltung des Weltfriedens
ምስል picture-alliance/dpa/Xinhua

ኬንያ በአብላጫ ድምፅ የተመድ የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት የተለዋጭ አባልነት መቀመጫ አገኘች። ትናንት ምሽት ኒዮርክ ውስጥ በተከፈተው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ በተካሄደው የድምጽ አሰጣጥ ስርዓት ላይ ኬንያ እና  ጅቡቲ ከምስራቅ አፍሪቃ ሃገራት የቀረቡ እጩ ሃገራት ነበሩ። በመንግሥታቱ ዋና ጽ/ቤት በተካሄደዉ በሁለተኛ ዙር ድምጽ አሰጣጥ ኬንያ ከ193 አባል ሀገራት የ129 ን ድጋፍን አግኝታ የሁለት ዓመት የተለዋጭ አባልነት መንበር ፀድቆላታል። የኮሮና ተኅዋሱ ስርጭትን ለመቆጣጠር ድምፅ አሰጣጡ ከፍተኛ የደኅንነት መመርያዎችን ተግባራዊ ያደረገም ነበር ተብሎአል። ከአራት ዓመታት በፊትም ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ ያልሆነ አባልነት ተመርጣ ነበር። በወቅቱም ኢትዮጵያ 185 ድምፅን በማግኘት ነበር አፍሪቃ ወክላ ተለዋጭ አባል መሆንዋ ይታወሳል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መስራች አባል የሆነችው ኢትዮጵያ በታሪኳ ውስጥ ሦስት ጊዜ የምክር ቤቱ ቋሚ ያልሆነ መቀመጫን ማግኘትዋ የሚታወቅ ነዉ። 

አዜብ ታደሰ 

ነጋሽ መሐመድ