ኬንያታ ሁለተኛ ዘመነ ሥልጣናቸዉን ጀመሩ
ማክሰኞ፣ ኅዳር 19 2010ማስታወቂያ
ኬንያ ዉስጥ ባለፈዉ ጥቅምት በተደረገዉ ድጋሚ ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ ያሸነፉት የሐገሪቱ ፕሬዝደንት ኡሁሩ ኬንያታ ዛሬ ቃለ መሐላ ፈፅመዉ የሁለተኛ ዘመነ-ሥልጣናቸዉን ሥራ በይፋ ጀምረዋል።ኬንያታ በአወዛጋቢዉ ምርጫ ማሸነፋቸዉን ያፀናዉ የሐገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ነዉ።ኬንያታ ዛሬ በዓለ ሲመታቸዉ ሲከበር በሀገሪቱ ሕዝብ መካከል ሰላምና መቀራረብን ለማውረድ እንደሚሰሩ ቃል ገብተዋል፡፡ይሁንና የኡሁሩ ኬንያታን ፕሬዘዳንትነት ‹‹አልቀበልም!›› ያለው የተቃዋሚዉ የብሔራዊ ላዕላይ ሕብረት (NASA-በምሕፃሩ) ደጋፊዎች እና ፖሊስ ርዕሠ-ከተማ ናይሮቢ ዉስጥ ተጋጭተዉ ነበር፡፡የናይሮቢዉ ወኪላችን ሐብታሙ ስዩም በዓለ ሲመቱን ተከታትሎት የላከልን ዘገባ አለን።
ሐብታሙ ስዩም
ነጋሽ መሐመድ
ሸዋዬ ለገሰ