ካራቱሪ ኩባንያ የቀረበበት አቤቱታ1 ግንቦት 2006ዓርብ፣ ግንቦት 1 2006ካራቱሪ የተባለዉ የህንድ ኩባንያ ጋምቤላ ዉስጥ ለእርሻ ሥራ የተሰጠዉን አንድ መቶ ሺህ ሄክታር መሬት ማልማትን ትቶ ከቀረጥ ነፃ የገቡ ማሽኖችን በማከራየት ሥራ መጠመዱን ሠራተኞች አመለከቱ።https://p.dw.com/p/1BxHMምስል DWማስታወቂያ ድርጅቱ ከ2000ዓ,ም ጀምሮ ከሰባት መቶሄክታር በላይ ጥቅጥቅ ደን በመመንጠር 20 ሺህ ኩንታል በቆሎ ካመረተ በኋላ ቀሪ ጊዜዉን ማሽን በማከራየት ተግባር መጠመዱ ተገልጿል። ኩባንያዉ በርካታ ሠራተኞቹን ከማባረሩ በተጨማሪ ደሞዝ ለመክፈልም ብዙ ደጅ ጥናት መኖሩን ከድርጅቱ ሠራተኞች ለዶቼ ቬለ ዘጋቢ ለዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር በዝርዝር ገልጸዋል። ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር፣ ሸዋዬ ለገሠ ሂሩት መለሰ