በ50 አመታት ከአፍሪቃ 1 ትሪሊዮን የሚገመት ገንዘብ ሸሽቷል
ረቡዕ፣ ግንቦት 30 2009ማስታወቂያ
የበለጸጉ ሃገራት እና የፋይናንስ ተቋማት ከአፍሪቃ ሸሽቷል ለተባለው ገንዘብ ተጠያቂ ናቸው ተብሏል። አብዛኛዉ ገንዘብ በተለይ ከምዕራብ አፍሪቃ እንደሚወጣ ነዉ የተገለጸዉ። የኮሚሽኑ አማካሪ አዲዬንካ አዴሚ ከአፍሪቃ ተመዝብሮ የሸሸው ገንዘብ ካልተመለሰ ለአኅጉሪቱ የእርዳታ ገንዘብ የሚፈይድላት ነገር የለም ሲሉ ተናግረዋል። የኤኮኖሚ ባለሙያዎች የመልካም አስተዳደር እጦት ለዝርፊያው ቀዳሚውን አስተዋፅዖ አበርክቷል ባይ ናቸው።
አክመል ነጋሽ
እሸቴ በቀለ
ሸዋዬ ለገሠ