ኦልመርት ስልጣናቸውን እንደሚለቁ ማስታወቃቸው25 ሐምሌ 2000ዓርብ፣ ሐምሌ 25 2000በሙስና ቅሌት ብዙ ሲወቀሱና ግፊት ሲደረግባችው የቆዩት የእሥራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ኤሁድ ኦልመርት የፓርቲና የመንግሥት ሥልጣናችውን እንደሚለቁ በትናንትናው ዕለት አስታውቀዋል። ኦልመርት ሥልጣናቸውን በፊታችን መሥከረም ወር አዲስ ለሚመረጠው የካዲማ ፓርቲያችው ሊቀ-መንበር እንደሚያስረክቡ ነው የገለጹት።https://p.dw.com/p/EoEPግፊት የተጠናከረባቸው የእስራኤል ጠቅላይ ሚንስትርምስል picture-alliance/ dpaማስታወቂያየሚገመተው የአገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዚፒ ሊቭኒ ወይም የመገናኛ ሚኒስትሩ ሻውል ሞፋስ ተተኪያቸው እንደሚሆኑ ነው። የተቃዋሚው ፓርቲ ግን ከጠቅላይ ሚኒስትር ለውጥ ይልቅ በሀገሪቱ አዲስ ምርጫ መካሄዱን ነው የሚሻው።