ኤቦላ እና የዓለም አቀፉ ምላሽ25 የካቲት 2007ረቡዕ፣ የካቲት 25 2007በምዕራብ አፍሪቃ የተከሰተውን የኤቦላ ስርጭት ለማብቃት የተደረገውን ዘመቻ ለመገምገም ትናንት በብራስልስ የተጠራው ዓለም ስብሰባ በበሽታው የተጎዱት ሀገራት ውስጥ የተኀዋሲው ስርጭት በጠቅላላ እስኪያቆም ድረስ መቀጠል እንዳለበት አሳሳበ።https://p.dw.com/p/1El2uምስል T. Charlier/AFP/Getty Imagesማስታወቂያ ለጋሽ መንግሥታት እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶችም ርዳታቸውን እና ድጋፋቸውን መስጠት እንዲያሳድጉ ተማፅኖዋል። ኤቦላ ከተከሰተ ካለፈው አንድ ዓመት ተኩል ውስጥ ወደ አስር ሺህ የሚጠጉ ሰዎች መሞታቸው፣ 24,000 ደግሞ ለወረርሽኙ እና ወረርሽኙ ላስከተለው ኤኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ችግር መጋለጣቸው ተገልጾዋል። ገበያው ንጉሤ አርያም ተክሌ ነጋሽ መሀመድ