ኤርትራውያን ተገን ጠያቂዎችና የስዊዘርላንድ ፍርድ ቤት ውሳኔ
ዓርብ፣ የካቲት 3 2009ማስታወቂያ
የስዊዘርላንድ ፍርድ ቤት ከአገራቸው በሕገ-ወጥ መንገድ መውጣታቸውን እንደበቂ ምክንያት በመቁጠር የኤርትራውያንን የተገን ማመልከቻ መቀበል ሊቆም ይገባል ውሳኔ አሳልፏል። ፍርድ ቤቱ ከአንድ ሳምንት በፊት ባሳለፈው ውሳኔ ለቀቅ ያለው የስዊዘርላንድ የተገን አቀባበል ፖሊሲ ምክንያታዊ አይደለም ብሏል።ባለፈው ዓመት ብቻ ከ5,000 በላይ ስደተኞች በስዊዘርላንድ የተገን ማመልከቻ አቅርበው ነበር። ከዚህ ቀደም ኤርትራውያን በስዊዘርላንድ ተገን ለማግኘት ከአገራቸው በሕገ-ወጥ መንገድ መውጣታቸውን መግለፅ ብቻ ይበቃቸው ነበር። መቀመጫውን በስዊዘርላንዷ የሴንት ጋል ከተማ ያደረገው ፌዴራል አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት አሰራሩን ከመረመረ በኋላ «ከኤርትራ በሕገ-ወጥ መንገድ መውጣት ብቻ ተገን ለማግኘት በቂ አይደለም» ሲል ውሳኔ አሳልፏል። ፍርድ ቤቱ በስዊዘርላንድ ተገን ካገኙ በኋላ ወደ ኤርትራ ለአጭር ጉብኝት የሚመላለሱ ስደተኞችን በማሳየነት ጠቅሷል። በዚህም ምክንያት በሕገ-ወጥ መንገድ ከአገራቸው የወጡ ኤርትራውያን የግድ እንግልት ደርሶባቸዋል ማለት አይደለም ከሚል ድምዳሜ ላይ መድረሱን ፍርድ ቤቱ አስታውቋል። ኤርትራዊውን አባ ሙሴ ዘርዓይ በፍርድ ቤቱ ውሳኔ ላይ አስተያየታቸውን ጠይቂያቸው ነበር።
እሸቴ በቀለ
ኂሩት መለሰ