ኢትዮጵያ ያልተለመደዉ ጉምና ጭጋግ
ሐሙስ፣ ሐምሌ 22 2013ማስታወቂያ
አዉሮጳና እስያን ያስጨነቀዉ ጎርፍና የዝንባ አደጋ ኢትዮጵያም መድረሱ እንደማይቀር የሚትሪዮሎጂ ባለሙያዎች እያስጠነቀቁ ነዉ። አዲስ አበባን ጨምሮ ደጋማዉን የኢትዮጵያ አካባቢ የጋረደዉ ጉምና ደመና የየአካባቢዉ ነዋሪን የዕለት ከዕለት እንቅስቃሴን እያጎለ ነዉ። የአዲስ አበባ ነዋሪዎች እንደሚሉት ዘንድሮ ያጋጠማቸዉ የጉም ግርዶሽና ቅዝቃዜ ከዚሕ ቀደም አይተዉት የማያዉቁት ዓይነት ነዉ። የኢትዮጵያ የሚትሪዮሎጂ ባለሙያዎች እንደሚሉት እይታን የሚጋርደዉ ጉም የበረራን እንቅስቃሴን ሊያዉክ ይችላል። በየአካባቢዉ የሚጥለዉና ይጥላል ተብሎ የሚጠበቀዉ ከባድ ዝናብ ደግሞ በርካታ አካባቢዎችን ሊያጥለቀልቅ እንደሚችል ባለሙያዎቹ እያስጠነቀቁ ነዉ።
ስዩም ጌቱ
ነጋሽ መሐመድ
ሸዋዬ ለገሠ