ኢትዮጵያ እና ግብፅን ያፋጠጠው አባይ ወንዝ
ቅዳሜ፣ መስከረም 10 2012ማስታወቂያ
ርዝመቱ 6650 ኪሎ ሜትር ይጠጋል። የተጠቃሚዎቹ ሕዝብ ቁጥር አንድ ላይ ቢደመር ወደ አምስት መቶ ሚሊዮን ይደርሳል፤ የአባይ (ናይል) ወንዝ። ኢትዮጵያ እና ግብፅን በዲፕሎማሲው መስክ በተደጋጋሚ በጠረጴዛ ዙሪያ እንዲገናኙ እና እንዲነጋገሩ አድርጓል። ከሰሞኑ ግን ግብፅ ይዛ የቀረበችው ሐሳብ ለኢትዮጵያ የሚዋጥ አይመስልም። ግብፅ የህዳሴው ግድብ 40 ቢሊዮን ኪዩቢክ ውኃ በየዓመቱ ይልቀቅ በሚል ያቀረበችው ሐሳብ በኢትዮጵያ የውኃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂኒየር ስለሺ በቀለ በኩል የማይሆን ነው የሚል ምላሽ ነው የተሰጠው። የናይል ወንዝ ለኢትዮጵያ፤ ግብጽ እና ሱዳን የመኖር እና ያለመኖር ጥያቄ እንደኾነ በበርካታ ታዛቢዎች ይነገራል። ሦስቱ ሃገራት ሰሞኑን ተገናኝተው ኢትዮጵያ በምትገነባው የህዳሴ ግድብ የውኃ አሞላል ላይ ከስምምነት ሳይደረስ ተለያይተዋል።
ይልማ ኃይለሚካኤል
ማንተጋፍቶት ስለሺ