ኢትዮጵያ እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ጥያቄ
ረቡዕ፣ ነሐሴ 25 2008ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ መንግሥት በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ ይወስዳል የሚባለውን የኃይል እርምጃ እና የሰብዓዊ መብት ጥሰት የሚያጣራ ዓለም ዓቀፍ መርማሪ ቡድን ወደ ሃገሪቱ እንዲገባ እንዲፈቅድ በድጋሚ ተጠይቋል ። ጥያቄው የቀረበው አምስት የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ ድርጅቶች ትናንት ባወጡት የጋራ መግለጫ ነው ። ጥያቄውን በጋራ ያቀረቡት ድርጅቶች አምነስቲ ኢንተርናሽናል ፣ «DEFEND DEFENDERS» የተባለው ለሰብዓዊ መብት ተከራካሪ ድርጅቶች እና ግለሰቦች ደህንነት የቆመው ድርጅት የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ማኅበር ፣ግንባር ቀደም የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ «FRONTLINE DEFENDERS» እና ዓለም ዓቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ፌደሬሽን የተባሉ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ ድርጅቶች ናቸው። የብራሰልሱ ወኪላችን ገበያው ንጉሴ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።
ገበያው ንጉሴ
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ