ኢትዮጵያ በአምነስቲ ኢንተርናሽናል ዓመታዊ ዘገባ
ማክሰኞ፣ መጋቢት 19 2015ማስታወቂያ
ዛሬ ለአንባቢዎች ይፋ የሆነው የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ዓመታዊ ዘገባ በጎርጎሪዮሱ 2022 ዓ.ም በዓለም ዙሪያ «እጅግ ገዳዩ ግጭት ዩክሬን ሳይሆን ኢትዮጵያ ነበር» ብሏል ። ዓመታዊ ዘገባው በደሉ የተፈጸመውም «ከዓለም የትኩረት አቅጣጫ ውጪ ነው» ነው ሲል አስነብቧል ። «ኢትዮጵያን ጨምሮ በሚያንማር እና በየመን በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ለተገደሉበት ግጭቶች ዓለም አቀፍ ተቋማት በቂ ምላሽ አልሰጡም» ሲልም ወቅሷል ። ያለፈው የጎርጎሪዮሱ ዓመት የሴቶች መብቶችም ያሽቆለቆለበት እንደሆነ ዓለም አቀፍ የመብት ተሟጋች ድርጅቱ ጠቅሷል ። ብዙ ግድያዎች እና ዝርፊያዎ፤ ጾታዊ ጥቃቶችን ጨምሮ በደሎች እና ሕገ ወጥ ወንጀሎች በበርካታ የዓለማችን አካባቢዎች ተካሂዷልም ብሏል ።
ይልማ ኃይለ ሚካኤል
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር