ኢትዮጵያ፤ መፈናቀልና ግድያ በምዕራብ ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል
ኢትዮጵያ፤ መፈናቀልና ግድያ በምዕራብ ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል
ኢትዮጵያ ፤ መፈናቀልና ግድያ በምዕራብ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል
ቻግኒ (አማራ ክልል) ውስጥ የሚገኘው የስደተኞች መጠለያ በቅርቡ ጥቃትና ግድያ ከበረታበት ከበኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለተፈናቀሉ የተዘጋጀ ነው። እዚህ የሠፈሩት አብዛኞቹ አማሮች ናቸው። ቤኒ ሻንጉል ክልል የሚኖሩት የሌሎቹ ብሔር አባላት በተለይም የሽናሻና ጉሙዝ ተወላጆች ጥቃቱን ቢፈሩም ከየአካባቢያቸዉ መውጣት ሰግተው አብዛኞቹ ጫካ ውስጥ ተሸሽገዋል።
ኢትዮጵያ ፤ መፈናቀልና ግድያ በምዕራብ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል
አብዛኞቹ ስደተኞች ያላቸውን ሁሉ ልብስና ገንዘባቸውን ሳይቀር ትተው ነው የወጡት። አንዳንዶች ለራሳቸው መተዳደሪያ ገቢ ለማግኘት በመጠለያ ጣቢያው መሠረታዊ የሚባሉ ነገሮችን ለመሸጥ ይሞክራሉ። ብስኩቶች፣ ዘይትና ቡና የመሳሰሉትን የምትሸጠው ስንቄ መንግሥቱ «ሥራ ለመጀመር እየሞከርኩ ነው።» ትላለች። «መኖሪያ መንደሬን ምንም ሳልይዝ ነው የለቀቅኩት፤ ወደዚህ የምመጣበት እንኳን አላገኘሁም።»
ኢትዮጵያ ፤ መፈናቀልና ግድያ በምዕራብ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል
ልጆቿን ለመከላከል ስትል እመቤት አበበ መጠለያ ጣቢያው ውስጥ ከመግባት አነስተኛ ቤት ተከራይታ ትኖራለች። ጠላ እየጠመቀች ትነግዳለች። ጥቃቱን ለማምለጥ ቤተሰቧ በአስከሬን ላይ ተረማምዶ ካመለጠ በኋላ አሁን አዲስ ሕይወት ለመጀመር እየሞከረች ነው። «ጥቃት አድራሾቹ ያገኙትን፦ አማራውን፣ ጉሙዙን፣ ሽናሻውንና ኦሮሞውን ሁሉ ነው የገደሉት። ለምን እዚያ እንደነበሩና መቼ ጥቃት እንዳደረሱ እንኳን አላውቅም» ትላለች የሆነውን ስታስታውስ።
ኢትዮጵያ ፤ መፈናቀልና ግድያ በምዕራብ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል
ትዕግሥት አዲሱ ጓደኞቿ ሲገደሉ በማየቷ ልጆቿን ይዛ አመለጠች። መንግሥት ራሳቸውን ለመከላከል እንዲችሉ በመንደሩ አንዳንድ ሚሊሺያዎችን አስታጥቃለሁ ብሏል። ሆኖም አብዛኞቹ ተሰዳጆች ፈፅሞ ወደዚያ ለመመለስ አያስቡም። «እንሞታለን እንጂ ወደዚያ ስፍራ መመለስ አንችልም» ትላለች ወጣቷ እናት። «በእኛ ላይ ያደረጉትን ተመልክተናል፤ እጅግ በርካታ መጥፎ ነገሮች ሲደረጉ ወደተመለከትንበት ትተነው ወደመጣንበት ቦታ መመለስ አንችልም።»
ኢትዮጵያ ፤ መፈናቀልና ግድያ በምዕራብ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል
የስደተኛ መጠለያ ጣቢያው ወደ ቻግኒ በሚወስደው ዋና መንገድ አቅራቢያ ከአጎራባች ክልል በ10 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ነው የሚገኘው። አጥር የለውም፤ በዚህ ምክንያትም የክልል ባለሥልጣናት የደህንነት ጉዳዮችን ያነሳሉ።
ኢትዮጵያ ፤ መፈናቀልና ግድያ በምዕራብ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል
ለምሳሌ እንደዚህ ቤተሰብ አንዳንድ ስደተኞች ከመጠለያው ውጭ ነው የሚኖሩት። የመንትዮቹ ወንዶች አባት እንደሚሉት በተመለከቱት ድርጊት ከገጠማቸው ድንጋጤ እስካሁን አልወጡም።
ኢትዮጵያ ፤ መፈናቀልና ግድያ በምዕራብ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል
ፓዌ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ ልዩ ወረዳ ነበር። የአሁኑ የኢትዮጵያ ክልል ሳይዋቀር በ1977ቱ ድርቅ ክፉኛ በተጎዱት አካባቢዎች ይኖሩ የነበሩት የአማራ ተወላጆች ያኔ ብዙ ሕዝብ ባልሰፈረበና ለም በሆነው በፓዌ ወረዳ የቀድሞዉ የኢትዮጵያ መንግሥት አስፍሯል። ፓዌ አሁን በመተከል ዞን ውስጥ ተካትቷል፤ ሆኖም የአማራ ብሔርተኛ ፓርቲዎች ወረዳዉ ወደ በፊት ይዞታው እንዲመለስ ይፈልጋሉ።
ኢትዮጵያ ፤ መፈናቀልና ግድያ በምዕራብ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል
በፀጥታው ችግር ምክንያት አሁንም ወደ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ መሻገር አስቸጋሪ ነው። ሆኖም ከገጠሩ አካባቢ ይልቅ ከተሞች የተሻለ ፀጥታ አላቸው። ጉዞ ለመቀጠል አነስተኛ አቶቡሶችም (ሚኒባሶች) ሆኑ ትላልቅ ተሽከርካሪዎች ወታደራዊ አጀብ መጠበቅ ይኖርባቸዋል። ማሪያ ጌርት ኒኩሌሱ