1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮጵያ ለመጀመርያ ጊዜ የተካፈለችበት የቬኒስያዉ ዓለምአቀፍ ኤግዚቢሽን

ሐሙስ፣ ሐምሌ 11 2016

ኢትዮጵያዊዉ ሰዓሊ ተስፋዬ ኡርጌሳ "ቅድመ ግምትና አብሮ መኖር" በሚል ርዕስ ቬኒስያ ዓዉደ ርዕይ ላይ ያቀረበዉ የስዕል ትርዒት በጣም መነጋገርያ ከነበሩ ትርዒቶች መካከል አንዱ ነው። የኢትዮጵያን የአሳሳል ጥበብ በመጠቀም ተስፋዬ ያቀረባቸዉ ስዕሎች በዘር ሃረግና ማንነት ላይ ያጠነጥናሉ። ኢትዮጵያ በቬኪስያ ስትቀርብ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑ ነዉ።

https://p.dw.com/p/4iU5j
ኢትዮጵያን ለመጀመርያ ጊዜ በቬኒስያ ዓለም አቀፍ ኤግዚሽን የወከለዉ ኢትዮጵያዊ ሰዓሊ ተስፋዬ ኡርጌሳ
ኢትዮጵያን ለመጀመርያ ጊዜ በቬኒስያ ዓለም አቀፍ ኤግዚሽን የወከለዉ ኢትዮጵያዊ ሰዓሊ ተስፋዬ ኡርጌሳምስል Tesfaye Urgessa

ኢትዮጵያ ለመጀመርያ ጊዜ የተካፈለችበት የቬኒስያዉ ዓለምአቀፍ ኤግዚቢሽን

ኢትዮጵያን ለመጀመርያ ጊዜ በቬኒስያ ዓለም አቀፍ ኤግዚሽን የወከለዉ ኢትዮጵያዊ  

«ኢትዮጵያዊዉ ሰዓሊ ተስፋዬ ኡርጌሳ "ቅድመ ግምት እና አብሮ መኖር" በሚል ርዕስ ቬኒስያ ቢየንናለ ዓዉደ ርዕይ ላይ ያቀረበዉ የስዕል ትርዒት በጣም መነጋገርያ ከነበሩ ትርዒቶች ውስጥ አንዱ ነው። የኢትዮጵያን የአሳሳል ጥበብ በመጠቀም ተስፋዬ ያቀረባቸዉ ስዕሎች በዘር ሃረግ  እና ማንነት ላይ ያጠነጥናሉ። ኢትዮጵያ በቬኪስያ ቢየንናለ በስዕል እግዚቢሽን በሰዓሊ ተስፋዬ ኡርጌሳ ስትወከል ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑ ነዉ።»

በጣልያን በቬኒስያ ከተማ ላይ በሁለት ዓመት አንድ ጊዜ በሚከፈተዉ ግዙፉ «ቬኒስያ ቢየንናለ» በተባለዉ የሥነ-ጥበብ ዓዉደ ርዕይ ላይ የስዕል ስራዎቹን ይዞ ኢትዮጵያን ወክሎ ስለቀረበዉ ስለ ሰዓሊ ተስፋዬ ኡርጌሳ ሰሞኑን እዚህ በአዉሮጳ ከቀረበዉ ዘገባ የተቀነጨበ ድምፅ የወሰደ ነበር ያደመጥነዉ።  በጣልያን ቬኒስያ ከተማ በየሁለት ዓመቱ የሚዘረጋዉ እና አንጋፋዉ የሥነ ጥበብ ኤግዚቢሽን ዘንድሮ ለ 60ኛ ጊዜ ለተመልካች ክፍት ሆንዋል። «የዉጭ ሃገር ዜጋ በሁሉ ቦታ » የሚል መርህን የያዘዉ የዘንድሮ ዓዉደርዕይ ላይ ታዋቂዉ ኢትዮጵያዊ ሰዓሊ ተስፋዬ ኡርጌሳ አገሩን ወክሎ ስዕሎቹን ሲያቀርብ አዉደርዕዩ ከጀመረ ከ 130 ዓመት በኋላ ለመጀመርያ ጊዜ የኢትዮጵያዉያ ስዕሎች የቀረቡበት ተብሏል። ሰዓሊ ተስፋዬም፤ እንደ አፍሪቃ ይህ መጀመርያችን ነዉ፤ ግን ገና ረጅም መንገድ ይጠብቀናል ሲል በሰጠዉ ቃለ ምልልስ ተናግሯል።

«ኢትዮጵያዊዉ ሰዓሊተስፋዬ ኡርጌሳ "ቅድመ ግምት እና አብሮ መኖር" በሚል ርዕስ ቬኒስያ ቢየንናለ ዓዉደ ርዕይ ላይ ያቀረበዉ የስዕል ትርዒት በጣም መነጋገርያ ከነበሩ ትርዒቶች ውስጥ አንዱ ነው። የኢትዮጵያን የአሳሳል ጥበብ በመጠቀም ተስፋዬ ያቀረባቸዉ ስዕሎች በዘር ሃረግ  እና ማንነት ላይ ያጠነጥናሉ። ኢትዮጵያ በቪኒስ ቢየንናለ በስዕል እግዚቢሽን በሰዓሊ ተስፋዬ ኡርጌሳ ስትወከል ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑ ነዉ።»

Tesfaye Urgessa  auf der Kunstbiennale in Venedig
ምስል Tesfaye Urgessa

በጣልያን በቬኒስያ ከተማ ላይ በሁለት ዓመት አንድ ጊዜ በሚከፈተዉ ግዙፉ «ቬኒስያ ቢየንናለ» በተባለዉየሥነ-ጥበብ ዓዉደ ርዕይ ላይ የስዕል ስራዎቹን ይዞ ኢትዮጵያን ወክሎ ስለቀረበዉ ስለ ሰዓሊ ተስፋዬ ኡርጌሳ ሰሞኑን እዚህ በአዉሮጳ ከቀረበዉ ዘገባ የተቀነጨበ ድምፅ የወሰደ ነበር ያደመጥነዉ።  በጣልያን ቪኒስ ከተማ በየሁለት ዓመቱ የሚጠረጋዉ እና አንጋፋዉ የሥነ ጥበብ ኤግዚቢሽን ዘንድሮ ለ 60ኛ ጊዜ ለተመልካች ክፍት ሆንዋል። «የዉጭ ሃገር ዜጋ በሁሉ ቦታ » የሚል መርህን የያዘዉ የዘንድሮ ዓዉደርዕይ ላይ ታዋቂዉ ኢትዮጵያዊ ሰዓሊ ተስፋዬ ኡርጌሳ አገሩን ወክሎ ስዕሎቹን ሲያቀርብ አዉደርዕዩ ከጀመረ ከ 130 ዓመት በኋላ ለመጀመርያ ጊዜ የኢትዮጵያዉያ ስዕሎች የቀረቡበት ተብሏል። ሰዓሊ ተስፋዬም፤ እንደ አፍሪቃ ይህ መጀመርያችን ነዉ፤ ግን ገና ረጅም መንገድ ይጠብቀናል ሲል በሰጠዉ ቃለ ምልልስ ተናግሯል።

ኢትዮጵያን ለመጀመርያ ጊዜ በቬኒስያ ዓለም አቀፍ ኤግዚሽን የወከለዉ ኢትዮጵያዊ ሰዓሊ ተስፋዬ ኡርጌሳ
ኢትዮጵያን ለመጀመርያ ጊዜ በቬኒስያ ዓለም አቀፍ ኤግዚሽን የወከለዉ ኢትዮጵያዊ ሰዓሊ ተስፋዬ ኡርጌሳምስል DW

«በዘንድሮዉ ቢየንናለ እንደምትመለከቱት ከአፍሪቃ ከሃምሳ አራት ሀገራት የተወከሉት ወይም የስነ-ጥበብ ስራዎቻቸዉን የሚያሳዩበት አዳራሽ ያላቸዉ፤ አሥራ አንድ ወይም አስራ ሁለት ሀገራት ብቻ ናቸዉ። ይህ ግን ጅማሮ ነዉ። ይሻሻላል፤  ግን ረጅም መንገድ ይጠብቀናል።»   

ኢትዮጵያን ለመጀመርያ ጊዜ በቬኒስያ ዓለም አቀፍ ኤግዚሽን የወከለዉ ኢትዮጵያዊ ሰዓሊ ተስፋዬ ኡርጌሳ
ኢትዮጵያን ለመጀመርያ ጊዜ በቬኒስያ ዓለም አቀፍ ኤግዚሽን የወከለዉ ኢትዮጵያዊ ሰዓሊ ተስፋዬ ኡርጌሳምስል Tesfaye Urgessa

ሰዓሊ ተስፋዬ ኡርጌሳን ያገኘነዉ በኢጣልያ ቬኒስያ ከተማ ላይ የስዕል ትርኢቱን አስተዋዉቆ ስራዉ ጋብ ካለለት በኋላ ባለፉት ሳምንታት ዉስጥ ነዉ። ጣልያን ቬኒስያ ከተማ ላይ ለ60ኛ ጊዜ ለተመልካቾች ይፋ የሆነዉ በዓለም አንጋፋዉ እና እዉቁ የሥነ-ጥበብ ትርኢት፤ ከተመሰረተ ዘንድሮ 130ኛ ዓመቱን ይዟል። በየሁለት ዓመቱ በሚከፈተዉ በዚህ ዓለም አቀፍ ዓዉደ ርዕይ ላይ ለየት ያሉ ስዕሎቹን ይዞ ለመጀመርያ ጊዜ ኢትዮጵያን ወክሎ ፤ የቀረበዉ ተስፋዬ የአዲስ አበባ ፤ የሳሪስ ልጅ መሆኑን የስዕል ትምህርትን የቀሰመዉም፤ እዝያዉ አዲስ አበባ ዉስጥ መሆኑን እንዲህ አጫዉቶናል።

ኢትዮጵያን ለመጀመርያ ጊዜ በቬኒስያ ዓለም አቀፍ ኤግዚሽን የወከለዉ ኢትዮጵያዊ ሰዓሊ ተስፋዬ ኡርጌሳ
ኢትዮጵያን ለመጀመርያ ጊዜ በቬኒስያ ዓለም አቀፍ ኤግዚሽን የወከለዉ ኢትዮጵያዊ ሰዓሊ ተስፋዬ ኡርጌሳምስል Tesfaye Urgessa

ሰዓሊ ተስፋዬ ኡርጌሳ በዚህ በምዕራቡ ዓለም በስዕሎቹ የታወቀ ሆንዋል፤ አሳሳሉ፤ የስዕል ጥበቡ ከሌሎች የኢትዮጵያዉያን ስዕሎች ለየት ያለ እንደሆን ብዙዎች ይናገራሉ። በጎርጎረሳዉያኑ 2009 ዓም የጀርመን የትምህርት ልውውጥ አገልግሎት ወይም በእንግሊዘኛ ምኅጻሩ(DAAD) የነጻ ትምህርት እድልን አግኝቶ በጀርመን ሃገር ሽቱትጋርድ ከተማ በሚገኝ የሥነ-ጥበብ አካዳሚ የከፍተኛ ትምህርቱን ተከታትሏል። ይሁንና ተስፋዬ በኢትዮጵያ የስዕል እዉቀቱን እንዴት አዳበረ? ወደዚህ ወደጀርመንስ እንዴት መጣ? ሰዓሊ ተስፋዬ ኡርጌሳ።

ግን እንደዉ መንግሥትን የባህል እና ስፖርት ጉዳይ የሚመለከታቸዉን አንድ ዓመት ፤ ስድስት ወር ያህል ወትዉተህ ደብዳቤ አጽፈህ የኢትዮጵያን ስም ከፍ አድርገህ አስጠርተሃል እና ይህ ጉዳይ እንዲቀጥል መቼም አሁን ባለስልጣናት ሊረዱት የሚገባ ይመስላል።

ኢትዮጵያን ለመጀመርያ ጊዜ በቬኒስያ ዓለም አቀፍ ኤግዚሽን የወከለዉ ኢትዮጵያዊ ሰዓሊ ተስፋዬ ኡርጌሳ
ኢትዮጵያን ለመጀመርያ ጊዜ በቬኒስያ ዓለም አቀፍ ኤግዚሽን የወከለዉ ኢትዮጵያዊ ሰዓሊ ተስፋዬ ኡርጌሳምስል Tesfaye Urgessa

130 ዓመት በሆነዉ እዉቁ የቬኒስያ የሥነ-ጥበብ አዉደርእይ በቬኒስያ ቢየንናለ ላይ ኢትዮጵያን ወክሎ ለመጀመርያ ጊዜ ስዕሎቹን ያቀረበዉ ሰዓሊ ተስፋዬ ኡርጌሳ፤ ስዕሎቹ እስከ ፊታችን  ህዳር 15 ቀን 2017 ዓም ድረስ፤ ለዓለም ህዝብ ለእይታ ክፍት ይሆናል። ከሁለት ዓመት በኃላ በቀጣይ በሚከፈተዉ የስዕል አዉደ ርዕይ ላይ ኢትዮጵያ እንድትሳተፍ የባህል ሚኒስትር ትብብሩን እንደ ዘንድሮዉ ሁሉ እንደሚያደርግ እናምናለን። ሰዓሊ ተስፋዬ ኡርጌሳን ለሰጠን ቃለ ምልልስ እያመሰገንን ሙሉ ስርችቱን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን።

አዜብ ታደሰ

ታምራት ዲንሳ