ኢትዮጵያዉን በሱዳን ወከባ በዛባቸዉ17 ሐምሌ 2000ሐሙስ፣ ሐምሌ 17 2000በሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያዉያን በሱዳን መንግስት ወታደሮች የሚደርስባቸዉ ጥቃትና ወከባ እየተባባሰ መሄዱ እየተሰማ ነዉ።https://p.dw.com/p/Ej8Dካርቱምምስል DW/Stefanie Ducksteinማስታወቂያበድንበር አቅራቢያ በገዳሪፍና ገላባት አካባቢ ለዓመታት በተለያዩ መስኮች ተሰማርተዉ ኑሮን እየገፉ ከሚገኙ ወገኖች መካከል በወታደሮች ከተደበደቡ፤ የፈላ ዉሃ ከተደፋባቸዉና፤ መሰል ጥቃት ከተፈፀመባቸዉ ሌላ በካርቱም መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች ይሰሩ የነበሩም እንዲሁ ከስራቸዉ በሱዳን መንግስት የሰራተኛ ጉዳይ ትዕዛዝ ተፈናቅለዋል።