ኢሰመጉ ረቂቅ የህትመት ውልን መቃወሙ
ሰኞ፣ ግንቦት 13 2004ማስታወቂያ
በቅርብ ጊዜ በማተሚያ ቤቶች ተዘጋጅቶ የቀረበው የውል ረቂቅ የህገ መንግሥቱን አንቀፅ የሚጥስ ነው ሲል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ አስታወቀ ። ኢሰመጉ የፕሬስ ነፃነት ይከበር በሚል ዛሬ ባወጣው መግለጫ መንግሥት ሁኔታውን መርምሮ መፍትሄ እንዲስጠም ጠይቋል ። ውሉን የኢትዮጵያ የግል ፕሬስ አሳታሚዎች በህገ መንግሥቱ ገደብ እንዳይጣልበት በተደነገገው የመናገር ነፃነት ላይ በህትመት ውል ኮንትራት ስም የተጣለ ቅድሚያ ምርመራ ነው ሲሉ ዓለም ዓቀፍ የጋዜጠኞች ማህበራትም እያወገዙት ነው ። የብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት በበኩሉ የህትመት ሥራ ደረጃ ያለው ውል ሥራን በጥራት ለመስራት ታስቦ እንጂ ቅድሚያ ምርመራ አይደለም ሲል ለዶቼቬለ መልስ ሰጥቷል ።
ታደሰ እንግዳው
ሂሩት መለሰ
ተክሌ የኋላ