አፍሪቃውያን ስደተኞች በበርሊን
ዓርብ፣ መጋቢት 12 2006ማስታወቂያ
ከአንድ ዓመት ተኩል በላይ መሀል በርሊን ውስጥ በድንኳን ተጠልለው የቆዩት አፍሪቃውያን ስደተኞች ከትናንት በስተያ አደባባዩን ለቀው ለመነሳት ተስማምተዋል ። እነዚሁ 476 ስደተኞች ከስፍራው ለመነሳት የተስማሙት ከከተማዋ አስተዳደር ጋር ከትናንት በስተያ በተደረሰበት ስምምነት መሠረት ነው ። በስምምነቱ ሰነድ ላይ እንደተገለፀው የበርሊን አስተዳደር ስደተኞቹ ያቀረቡለትን ጥያቄዎች ለመመለስ ቃል ገብቷል ።እርዳታ ሰጭዎች አስፈላጊውን እንክብካቤ እንዲያደርጉላቸውም ፈቃደኝነቱን ገልጿል ። ስምምነቱ በመፈረሙ አስተዳደሩ ደስታውን ሲገልፅ አንዳንድ ስደተኞች ደግሞ ስምመነቱ ብቻውን በቂ አይደለም ሲሉ ቅሪታቸውን በመግለፅ ተጨማሪ ጥያቄዎችን ሰንዝረዋል ። ይልማ ኃይለ ሚካኤል ዝርዝር አገባ አለው ።
ይልማ ኃይለ ሚካኤል
ሂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ