አፍሪቃዉያን ስደተኞች በማልታ
ረቡዕ፣ ኅዳር 12 2005ማስታወቂያ
250 ስደተኞች ለችግር ተጋልጠዉ በማልታ የባህር ጠረፍ ጠባቂዎች ህይወታቸዉ ተርፏል። ስደተኞቹ ሊቢያ ቤንጋዚ ላይ ለመኖር የሚያስችላቸዉ ህጋዊ ፈቃድ ስለሌላቸዉ ከታሰሩበት ወህኒ ለመዉጣትና ወደአዉሮጳ ሀገሮች ለመጓዝ ገንዘብ እንዲከፍሉ ማንነታቸዉ ባልታወቀ የሊቢያ ዜጎች የተጠየቁ ሲሆን ከፍለዉ የወጡትም ቢሆኑ ቤንጋዚ ላይ በአንዲት ስፍራ ታግተዉ ለመቆየት ተገደዋል። በዚሁ ስፍራም የአንድ ስደተኛ ህይወት አልፏል። በማልታ ባህር ጠረፍ ጠባቂዎች ርዳታ የተረፉት ወገኖች ለተመ የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን ባለስልጣናት እንደገለፁት ለሁለት ቀን የሚሆን ዉሃ ምግብ የሰጧቸዉ ህገወጥ ሰዉ አሸጋጋሪዎች በአነስተኛ ጀልባ ጭነዉ ባህር ላይ ነዉ የለቀቋቸዉ።
ተኽለእግዚ ገብረኢየሱስ
ሸዋዬ ለገሠ
አርያም ተክሌ