አዲስ አዉሮፕላን በአዲስ አበባ
ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 3 2004ማስታወቂያ
የአዲስ አበባ አዉሮፕላን ማረፊያ ዛሬ ከአዲስ አዉሮፕላን ጋር ተዋዉቃለች።የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአምስት አመት በፊት ያዘዘዉ ድሪም-ላይነር ቦይግ 787 የተሰኘዉ የአዉሮፕላን ዓይነት ዛሬ አዲስ አበባ ዉስጥ ለአይታ ቀርቧል።የኢትዮጵያ አየር መንገድ የገዛዉን አዉሮፕላን ገና አልተረከበም። የአዉሮፕላኑን አይነት ለማስተዋወቅ አዲስ አበባ ያረፈዉን አዉርፕላን ከተመለከቱት ጋዜጠኞቹ ጌታቸዉ ተድላ ሐይለ ጊዮርጊስ አንዱ ነዉ።
ጌታቸዉ ተድላ ሐይለ ጊዮርጊስ
ነጋሽ መሐመድ
አርያም ተክሌ