የአዲስ አበባ ጅቡቲ የባቡር መስመር
ረቡዕ፣ መስከረም 25 2009ማስታወቂያ
አዲስ አበባን ከጅቡቲ የሚያገናኘው አዲሱ የባቡር መስመር ዛሬ ተመረቀ ። በቻይና ኩባንያዎች የተሰራው ይኽው የባቡር መስመር ለኢትዮጵያ ልማት ብዙ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት የኢትዮጵያ የባቡር መንገድ ኮርፖሬሽን ባለሥልጣናት ዛሬ በተካሄደው የምረቃ ስነ ስርዓት ላይ ተናግረዋል ። 656 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ይኽው የባቡር መስመር ስራ ሲጀምር ቀድሞ ሦስት ቀናት ይፈጅ የነበረውን ጉዞ ወደ 12 እና 15 ሰዓት ዝቅ እንደሚያደርገው ተነግሯል ። ግንባታው 3.4 ቢሊዮን ዶላር የፈጀው ይኽው የባቡር መስመር ሥራውን ሙሉ ለሙሉ ሲጀምር በቀን 5,600 ሰዎች እና 3500 ቶን ቁሳቁሶችን ማመላለስ ይችላል ተብሏል ። በምረቃው ስነ ስርዓት ላይ የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ተገኝቷል ።
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ