1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አንድ ለአንድ፤ ከፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሃሐ ጋር

ዓርብ፣ ጥር 30 2017

« እኔ በእውነቱ በሥራዬ ጥሩንባ የምነፋ ሰው አይደለሁም» ፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሐቅ

https://p.dw.com/p/4q6ic
Symbolbild Friedenstaube
ምስል Fotolia/chris-m

አንድ ለአንድ፤ ሙሁራን ሰላምን በማስፈን ሚናቸውን እየተወጡ ነውን?

ፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሐቅ በሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ የአፍሮ አሜሪካን ጥናት መሥራች ሲሆኑ የትምህርት ክፍሉ በ1969 ሲፈጠር የመጀመሪያው ፕሮፌሰር ነበሩ ። ስለ አይሁድና ስለ ጥንታዊት ኢትዮጵያ ኪነጥበብ ጽሑፎች በርካታ ጽሑፎችንና መጻሕፍትን አዘጋጅተዋል ። በአሁኑ ወቅት ኒው ጀርሲ በሚገኘው ፕሪንስተን የሴሜቲክ ጥናት ተቋም ዳይሬክተር ሲሆኑ፣ የአፍሪካ ቀንድ የሰላም እና ልማት ኮሚቴ ሊቀመንበር እና የየመን አይሁድ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ናቸው ፡ ፡ በፕሪንስተን ዩኒቨርሲቲ ፣ በዕብራይስጥ ዩኒቨርሲቲ ፣ በፔንሲልቫንያ ዩኒቨርሲቲ ፣ በሐቫርድ ኮሌጅና በሌሎች የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አስተምረዋል ።
ፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሐቅ ቢያንስ ሰባት ቋንቋዎችን በማወቃቸውም ይታወቃሉ ። ከሁሉም በላይ ግን መለያው የሆነውን ባህላዊ የኢትዮጵያ ልብስ በመልበስ ይታወቃል ። ባለፉት ዓመታት ለኢትዮጵያ ካበረከቱት ዘርፈ ብዙ አስተዋጽኦዎች መካከል የሃገር ሽማግሌ በመሆን በሃገሪቱ በተለያዩ ጊዚያት በተከሰቱ ፖለቲካዊ ትኩሳቶች መፍትሔ በማፈላለግ ይታወቃሉ። አሁን ባለው ምስቅልቅል ሚናዎትን እየተወጡ ነው ወይ? የሚል ጥያቄን ጨምሮ የሙሁራንና የሐገር ሽማግሌዎች ሚናን በተመለከተ አጭር ቆይታ አድርገናል። የድምጽ ማዕቀፉን በመጫን ሙሉ ዝግጅቱን እንድታዳምጡት በአክብሮት እንጋብዛለን።


ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር
ነጋሽ መሐመድ