አስተያየት በመገናኛ ብዙሃን ም/ቤት ምሥረታ
ዓርብ፣ ጥር 6 2008ማስታወቂያ
ከምሥረታው በፊት በርካታ አጨቃጫቂ ጉዳዮች ይቀርቡበት የነበረው የመገናኛ በዙሃን ምክር ቤት ከምሥረታው በኋላም ቢሆን ሁሉንም ጋዜጠኞችና የመገናኛ ብዙሀን ድርጅቶችን ይሁንታ ያገኘ አይመስልም። ገለልተኛ የሆኑም ሆነ አፍቃሬ መንግሥት የሆኑ አንዳንድ የመገናኛ ብዙሀን ከምክር ቤቱ አባልነት ራሳቸውን አግልለዋል።
ቀደም ባሉ ጊዜያት ምክር ቤቱን ለመመሥረት ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ጋዜጠኞችም በጥርጣሬ ይመለከቱታል። ለጋዜጠኞች የሚሟገቱ እንደ ሲፒጄ ያሉ ድርጅቶችም ምሥረታዉን በርቀት እየተከታተሉት እንደሆነ ተነግሯል። ከዋሽንግተንዲሲ ወኪላችን ዝርዝሩን ልኮልናል።
ናትናኤል ወልዴ
ሸዋዬ ለገሠ
ኂሩት መለሰ