አሳሳቢው የኑሮ ውድነት
ረቡዕ፣ የካቲት 24 2013ማስታወቂያ
በኢትዮጲያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየጨመረ የሚገኘው የሸቀጦች ዋጋ፣ የኑሮ ውድነት እንዲባባስ ምክንያት እየሆነ ይገኛል። የዋጋ ጭማሪው በተለይ አብዛኛው የማህበረሰብ ክፍል ሸማች በሆነባቸው የከተሞች አካባቢ የዜጎች እለታዊ ኑሮ እንዲከብድ አድርጎታል ነው የሚባለው። በሐዋሳ ከተማ የመገበያያ ስፍራ ለግብይት የወጡ ሸማቾች እና ሻጮች የኑሮ ውድነቱ እንደከበዳቸው ገልጠዋል። የምጣኔ ሐብት ጉዳዮች ምሁራን የችግሩን ምንጭ ከመሠረቱ ለማወቅ በመረጃ ላይ የተደገፈ ጥናት አስፈላጊነቱ ላይ አጽንዖት ሰጥተዋል። ያም ሆኖ ግን የምርት ፍላጎት እና አቅርቦት አለመጣጣም፣ የሥራ አጥ ዜጎች መበራከት፣ የሕዝብ ቊጥር እድገት መጨመር እና የማምረቻ ግብአቶች የዋጋ ንረት ለኑሮ ውድነት መባባሱ እንደምክንያትነት ይጠቅሳሉ። መንግሥት ችግሮቹን በሦስት መንገዶች መቆጣጠር እንደሚችል ምሁራን ጠቅሰዋል። ሙሉውን ዝግጅት በድምጽ ማዕቀፉ ማድመጥ ይቻላል።
ሸዋንግዛዉ ወጋየሁ
ማንተጋፍቶት ስለሺ