አምባሳደር ዮአኺም ሽሚት ሲታወሱ
በኢትዮጵያ የጀርመን እና የአፍሪቃ ኅብረት አምባሳደር በመሆን ያገለገሉት ዮአኺም ሽሚት በቅርቡ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። በአፍሪቃ ኅብረት የጀርመን አምባሳደርም የነበሩት ዮአኺም ሽሚት ወደ ኢትዮጵያ በአምባሳደርነት ተሾመዉከመሄዳቸዉ አስቀድመዉ በቦስኒያ ሄርዞጎቭኒያ እና ሰርቢያም በአምባሳደርነት አገልግለዋል።
ለኢትዮ ጀርመን ግንኙነት የሽሚት አስተዋጽኦ
አምባሳደር ዮአኺም ሽሚት፤ የጀርመን መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል በጥቅምት 2009ዓ,ም ኢትዮጵያን በጎበኙበት ወቅት ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ እና ከሌሎች የጀርመን ልዑካን ጋር።
የጀርመን መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ተሳትፎ
በጀርመናዊዉ ሩዲገር ኔበርት የተቋቋመዉ የጀርመኑ መንግሥታዊ ያልሆነ ግብረ ሠናይ ድርጅት ታርጌት፤ በኢትዮጵያ አፋር ክልል በኩነባ ወረዳ በፈረስ ደገ ቀበሌ ገበሬ ማኅበር ዉስጥ ያስገነባዉን ክሊኒክ አስመርቋል። በወቅቱ በምረቃዉ ሥርዓት ላይ በመገኘት ለበዓሉ ድምቀት ከሰጡት አንዱ በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር የነበሩት ዮአኺም ሽሚት ነበሩ።
በአፋር ክልል የክሊኒክ ምረቃ
በጀርመን የኢትዮጵያ አምባሳደር የነበሩት ዮአኺም ሽሚድት በአፋር ክልል በኩነባ ወረዳ በፈረስ ደገ ቀበሌ ገበሬ ማኅበር ዉስጥ ታርጌት ያስገነባዉ ክሊኒክ ምረቃ ላይ ንግግር ሲያደርጉ።
ለማኅበራዊ ተሳትፎ ሽልማት
አምባሳደር ዮአኺም ሽሚት የጀርመኑ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ታርጌት አፋር ክልል በኩነባ ወረዳ ፈረስ ደገ ቀበሌ ገበሬ ማኅበር ዉስጥ ያስገነባዉ ክሊኒክ በተመረቀበት ዕለት የክልሉ ኗሪ ኅብረተሰብም አክብሮቱን በሽልማት እንዲህ ከክልሉ ኃላፊዎች አንዱ በሆኑት ባለስልጣን ገልጿል።
አነጋጋሪዉ የአየር ንብረት ለዉጥ ጉዳይ
በአዲስ አበባዉ የጀርመን ኤምባሲ የአዉሮጳ ኅብረት የአየር ንብረት ለዉጥ ጉዳይ ዉይይት ላይ አምባሳደር ዮአኺም ሽሚት የበኩላቸዉ ሃሳብ ሲያቀርቡ።
ጀርመን ሆሎኮስትን አትረሳም
አዲስ አበባ ላይ በተመድ የኤኮኖሚ ኮሚሽን አዳራሽ አይሁዳዉያን የተፈጁበት የሆሎኮስት እልቂት መታሰቢያ ዝግጅት ሲካሄድ አብሳደር ዮአኺም ሽሚት በኢትዮጵያ የእስራኤል አቻቸዉ ከሆኑት ከአምባሳደር በላይነሽ ዘቫዲያ ጋር።
የጀርመን ዉሕደት 25ኛ ዓመት በአዲስ አበባ
ምሥራቅ እና ምዕራብ ጀርመን የተዋሃዱበት 25ኛ ዓመት በኢትዮጵያ ሲከበር አምባሳደር ዮአኺም ሽሚት የጀርመን ኤምባሲ ባዘጋጀዉ ልዩ የስፖርት ዉድድር ላይ በመገኘት ከታዋቂዉ ኢትዮጵያዊ አትሌት ኃይሌ ገብረ ሥላሴ ጋር በመሆን ለአሸናፊዎች ሽልማት ሲሰጡ።
የብዙዎችን ቀልብ የሚስበዉ እግር ኳስ
ዩሮ 2016 የእግር ኳስ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታን በብዙዎች ተወዳጅነት የነበራቸዉ አምባሳደር ዮአኺም ሽሚት በአዲስ አበባዉ የጀርመን ትምህርት ቤት ባለቤታቸዉን ጨምሮ ከበርካቶች ጋር ተሰብስበዉ ነበር የጀርመንን እና የኔዘርላንድስን ጨዋታ የተከታተሉት።
አምባሳደር ሽሚት በቦስኒያ ሄርዞጎቭኒያ
አምባሳደር ዮአኺም ሽሚት በቦስኒያ ሄርዞጎቭኒያ የጀርመን አምባሳደር በነበሩበት ወቅት ከቦስኒያ የፋይናንስ ሚኒስትር ድራጋን ቪራንኪች ጋር ፊርማቸዉን ሲያኖሩ።
የጀርመንን ዉሕደት ያዘከረዉ የሙዚቃ ድግስ
በጎርጎሪዮሳዊዉ 2010ዓ,ም ጥቅምት ወር ሳሪየቮ ላይ የጀርመን የዉሕደት ቀን ሲታሰብ የሙዚቃ ድግስ ተዘጋጅቶ ነበር። በዚያ የሙዚቃ ኮንሰርት ላይ በወቅቱ በቦስኒያ ሄርዞጎቭኒያ የጀርመን አምባሳደር ዮአኺም ሽሚት ተገኝተዋል።
በሰርብሬኒስካ ለሙታን መታሰቢያ የአበባ ጉንጉን
የሰርብሬኒስካ እልቂት ወይም የዘር ፍጅት በመባል ይታወቃል፤ በጎርጎሪዮሳዊዉ 1995ዓ,ም 8 ሺህ ሙስሊሞች አብዛኞቹም አዋቂ እና ሕጻናት ወንዶች ሰርብሬኒካ በምትባለዉ ከተማ አካባቢ በቦስኒያዉ ጦርነት ወቅት አልቀዋል። አምባሳደር ዮአኺም ሽሚት በከተማዋ ተገኝተዉ ለሙታኑ የአበባ ጉንጉን በማስቀመጥ የሕሊና ጸሎት አድርሰዋል።
ታታሪና ተወዳጅ የነበሩት አምባሳደር ዮአኺም ሽሚት
በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር የነበሩት ዮአኺም ሽሚት በተግባቢነታቸዉ እና በማኅበረሰቡ ዉስጥ ባደረጉት ተሳትፎ ዉዴታን እና ዝናን አትርፈዋል። ሸዋዬ ለገሠ/አዜብ ታደሰ
በኢትዮጵያ የጀርመን እና የአፍሪቃ ኅብረት አምባሳደር በመሆን ያገለገሉት ዮአኺም ሽሚት ከዚህ ዓለም በሞት መለየት የተሰማዉ በድንገት ነዉ። በአፍሪቃ ኅብረትም የጀርመን አምባሳደር የነበሩት ዮአኺም ሽሚት ወደ ኢትዮጵያ በአምባሳደርነት ተሾመዉ የሄዱት በጎርጎሪዮሳዊዉ የዘመን ቀመር ከሐምሌ 2014 ጀምሮ ነበር። ወደ ኢትዮጵያ ከመሄዳቸዉ አስቀድመዉም በቦስኒያ ሄርዞጎቭኒያ እና ሰርቢያም በአምባሳደርነት አገልግለዋል። አምባሳደር ዩአኺም ሽሚት በኢትዮጵያ እጅግ ተወዳጅ እና ታዋቂ እንዲሁም ከማኅበረሰቡ ጋር እጅግ ቅርበት አላቸዉ ከሚባሉ የዉጭ ሃገራት አምባሳደሮች ቀዳሚዉን ስፋራ የሚይዙ ነበሩ።