አሜሪካ የምትከተለው የአፍሪቃ ፖሊሲ
ሰኞ፣ ሰኔ 17 2005ማስታወቂያ
የዮናይትድ እስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ጀርመንን ብቻ ጎብኝተው ማብቃት የፈለጉ አይመስልም። በሚመጣው ሳምንት ወደ አፍሪቃ ይጓዛሉ። እዛም ሶስት ሀገራትን፤ ሴኔጋል፣ ደቡብ አፍሪቃ እና ታንዛንያን ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል። በባራክ ኦባማ በፕሬዚዳንትነት መመረጥ በርካታ አፍሪቃውያን መደሰት ብቻ ሳይሆን ትንሽም ቢሆን ፕሬዚዳንቱ ለጥቁሮች አህጉር አፍሪቃም ይተርፋሉ ብለው ተስፋ ጥለውባቸው ነበር። ባራክ ኦባማ ስልጣን ከያዙ ካለፉት 5 ዓመታት ወዲህ ለመሆኑ ዮኤስ አሜሪካ የምትከተለው የአፍሪቃ ፖሊሲ ምን ይመስላል? የዛሬው የእንወያይ ዝግጅት ርዕስ ነው። የዋሽንግተን ዲሲ ዘጋቢያችን አበበ ፈለቀ ውይይቱን መርቷል።
አበበ ፈለቀ
ልደት አበበ