አሜሪካ ኢትዮጵያን ከአግዋ የቀረጥ ነፃ ንግድ የመሰረዝ ስጋት
ሐሙስ፣ ጥቅምት 4 2014ማስታወቂያ
ዩናይትድ ስቴትስ በሰሜን ኢትዮጵያ ተባብሶ ለቀጠለው ግጭት መልስ ለመስጠት የምጣኔ ሐብት ማዕቀብን ጨምሮ ሌሎች አማራጮችን በማጤን ላይ እንደምትገኝ ማስታወቋን ተከትሎ በአገሪቱ የኢንዱስትሪ ዘርፍ ላይ የስጋት ድባብ እየጣለበት ይገኛል።
የማዕቀብ ውሳኔው ገቢራዊ ከሆነ የአሜሪካ መንግስት በሰጠው ከቀረጥ ነፃ የንግድ ማበረታቻን መጠቀም ወደ ኢትዮጲያ የገቡ የውጭ ኩባንያዎችንና በእንዱስትሪዎቹ ተቀጥረው የሚሰሩ በአነስተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ዜጎችን ሊጎዳ እንደሚችል ከወዲሁ እየተነገረ ይገኛል።
ሸዋንግዛዉ ወጋየሁ
አዜብ ታደሰ
ኂሩት መለሰ