ፖለቲካሰሜን አሜሪካ
አሜሪካ፦የ9/11 ጥቃት እና ያስከተለው ውጥንቅጥ
ሰኞ፣ መስከረም 3 2014ማስታወቂያ
አሜሪካ ባለፈው ቅዳሜ በጎርጎሮሳዊው አቆጣጠር መስከረም 11 ቀን 2001 ዓ.ም የተፈጸመውን እና 3, 000 ገደማ ሰዎች የተገደሉበትን የሽብር ጥቃት አስባ ውላለች። በኒው ዮርክ ከተማ የጥቃቱ ፈጻሚዎች ባገቷቸው አውሮፕላኖች የወደሙት የዓለም የንግድ ማዕከል መንትያ ሕንፃዎች ይገኙ በነበረበት የማንሐታን አካባቢ በተካሔደው የመታሰቢያ መርሐ-ግብር ፕሬዝደንት ጆ ባይደን፣ የቀድሞዎቹ ፕሬዝዳንቶች ባራክ ኦባማ እና ቢል ክሊንተን ተገኝተዋል።
በወቅቱ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት የነበሩት ጆርጅ ደብሊው ቡሽ በሽብር እና አሸባሪዎች ላይ ጦርነት ያወጁት ከዚህ ጥቃት በኋላ ነበር። ጥቃቱ በአሜሪካ ላይ ካደረሰው ጉዳት ባሻገር በአፍጋኒስታን እና በኢራቅ የጦርነት መነሾ ሆኗል። በዛሬው የማሕደረ ዜና መሰናዶ ገበያው ንጉሴ ከ20 አመታት በፊት የተፈጸመው ጥቃት እና ጥቃቱን የተከተለውን ውጥንቅጥ ይቃኛል።
ገበያው ንጉሴ
እሸቴ በቀለ