የአሜሪካን ወቀሳ
ዓርብ፣ ሐምሌ 28 2009ማስታወቂያ
ከ 14 ሚሊዮን በላይ ዜጎቻቸው ለረሀብ የተጋለጡባቸው የአፍሪቃ መንግሥታት ችግሩን ለመከላከል አስቀድመው ባለመዘጋጀት ተወቀሱ። በተመድ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሰደር ኒኪ ሃሊ በዚህ ሳምንት እንዳሉት አፍሪቃ የዓለማችን የረሀብ እና የግጭቶች ማዕከል መሆኗ የመሪዎቿ የጋራ ጥፋት ነው። አምባሳደሯ የኮንጎ ዴሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ በቀጣዮቹ ዓመታት የመንግሥታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብት ተመልካች መስሪያ ቤት አባል እንድትሆን የአፍሪቃ ሀገራት የሰጡትን ድጋፍም አስገራሚ ብለውታል። በአስተያየቱ ላይ ለዶቼቬለ ማብራሪያ የሰጡ የሰብዓዊ መብት እና የዓለም አቀፍ ህግ መምህር በአፍሪቃ ተጠያቂነት አለመኖሩ የችግሩ መንስኤ መሆኑን ገልጸው የዩናይትድ ስቴትስ መርህም ወጥ አለመሆንም የችግሩ አካል ነው ብለዋል። መክብብ ሸዋ ከዋሽንግተን ዲሲ ዝርዝሩን አዘጋጅቷል።
መክብብ ሸዋ
ኂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ