አሌ ልዩ ወረዳ «ታጣቂዎች» ባደረሱት ጥቃት አምስት ሰዎች ተገደሉ
ሐሙስ፣ ጥቅምት 18 2014ማስታወቂያ
ለጊዜው ማንነታቸው በውል ያልተገለጸ ታጣቂዎች ባለፉት ሁለት ተከታታይ ቀናት በሶስት ቀበሌዎች ዘልቀው በመግባት ሶስት ሰላማዊ ሰዎች ላይ ጥቃት አድርሰው መግደላቸውን በስፍራው የነበሩ የአይን እማኞች ገልጸዋል። ሁለቱ ሰዎች ደግሞ እርስ በእርስ ተታኩሰው መገዳደላቸው ነው የተነገረው።
በታጣቂዎቹ ጥቃት ግድያ መፈጸሙን ለዶቼ ቬለ (DW) ያረጋገጡት የአሌ ልዩ ወረዳ ፖሊስ ጽህፈት ቤት ሃላፊዎች በበኩላቸው በድርጊቱ ፈጻሚዎች ላይ በፀጥታ ሀይሎች ክትትል እየተደረገ እንደሚገን ገልጸዋል
ሸዋንግዛዉ ወጋየሁ
ታምራት ዲንሳ
እሸቴ በቀለ