ቻይና፤ በቃጠሎ 38 ሰዎች ሞቱ
ማክሰኞ፣ ኅዳር 13 2015ማስታወቂያ
በማዕከላዊ ቻይና በሚገኝ አንድ ፋብሪካ ውስጥ በደረሰ የእሳት አደጋ 38 ሰዎች መሞታቸዉ ተነገረ። በቻይናዋ ሄናን ግዛት በምትገኘዉ በአናንግ ከተማ በተነሳዉ ቃጠሎ ሌሎች ሁለት ሰዎች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውን የቻይና መንግስት መገናኛ ብዙኃኖች ዘግበዋል። የእሳት አደጋዉ የመገጣጠምያ መሣሪያዎችን "ሕገ ወጥ" በሆነ መንገድ በመጠቀም መቀስቀሱን የመንግሥት መገናኛ ብዙኃኖች ዘግበዋል። ከስፍራዉ በወጡ ነገርግን ያልተረጋገጡ በተባሉ ዘገባዎች መሰረት ፤ አካባቢዉ ላይ የኬሚካል ቁሳቁሶች ተከማችተዉ ነበር። በቻይና አብዛኛውን ጊዜ በቸልተኝነት አልያም የደህንነት መመሪያዎችን ባለመከተል ምክንያት በኢንዱስትሪ አካባቢዎች ይህን መሰል የእሳት አደጋና እንደሚከሰተም ተመልክቷል።
አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሐመድ